“በህዳሴ ግድቡ ያሳረፍነውን አሻራ በሀገራዊ ምክክሩም እንደግማለን”
********************
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያሳዩትን የታሪክ አሻራ በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ በመድገም ጠንካራ ሀገር በመገንባት ለትውልድ ለማስተላለፍ የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ሲሉ በምክክር ጉባኤው ላይ እየተመካከሩ የሚገኙ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጎብኘት የተሰማቸውን ደስታና ኩራት ገልፀዋል፡፡
ከሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ የመጡት ተመካካሪ አድጎልኝ መኮንን በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግሥት ሠራተኛ በነበሩበት ወቅት የ400 ብር ቦንድ ገዝተው አስተዋጽኦ ያደረጉበት ግድብ ተጠናቆ በማየታቸው ጥልቅ የደስታ ስሜት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
"ዓባይ ግንድ ይዞ ይዞራል" መባሉ ቀርቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ትልቅ የብርሃን ምንጭ መሆን መቻሉ ታላቅ ኩራት ነው ብለዋል።
አሁን ደግሞ ከመላ ኢትዮጵያና ከውጭ ሀገር የተውጣጡ አራት ሺህ ዜጎች በመካከር ላይ መሆናቸውን አውስተው፤ በምክክር ጉባኤው ላይ ስለሀገራቸው ጉዳይ በነጻነት የሚመካከሩበትን ትልቅ ታሪካዊ ዕድል ለመጀመሪያ ጊዜ አግኝተናል ሲሉ ገልፀዋል።
ዜጎች በመመካከር ጠንካራ ሀገር ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረገው የሰለጠነ የምክክር ሂደት የሚያስደስት ሆኖ እንዳገኙትም ጠቅሰዋል፡፡
ከሰዊድን የመጡት ተመካካሪ መቅደስ ወርቁ በበኩላቸው፤ በግድቡ ግንባታ ወቅት በውጭ ሀገር ሲያስተባብሩ መቆየታቸውን ገልጸው፤ አሁን ግድቡ ተጠናቆ በአካል ማየት በመቻላቸው ደስታና ኩራት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
በግድቡ የተሰራው ድንቅ ተግባር የኢትዮጵያውያንን ገድል እና ዳግማዊ ዓድዋ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ከእንግሊዝ ሀገር የመጡት ተመካካሪ ኡስታዝ ሙክታር ጀማል፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉብኝት ወቅት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።
ከካናዳ ቶሮንቶ የመጡት ተመካካሪ ጌትነት ሃይሉ በበኩላቸው፤ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የወር ደመወዛቸውን ሳይቀር በማዋጣት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በግድቡ ግንባታ ወቅት ዓለም አቀፍ ተቋማት ብድር በመከልከል ጫና ቢፈጥሩም፣ ኢትዮጵያውያን ግን በጋራ በመተባበር ግድቡን በራሳቸው አቅም መገንባታቸው ታሪካዊ ድል መሆኑን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በአሁኑ ወቅት ለትውልድ ጠንካራ ሀገር ለማስተላለፍ የሚያስችላቸውን የምክክር ሂደት መሳተፍ በመቻላቸውም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
የምክክር ሂደቱ ውጤት አብሮነታችንን በማጽናት በተጠናከረ መልኩ በጋራ ለልማት መነሳሳት እንደሚቻል እምነታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፤ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ በመግዛት፣ በስጦታ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስለግድቡ በመከራከር ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ግድቡ የኤሌትሪክ ሃይል ያልደረሳቸው ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ለከባድ ኢንዱስትሪዎች እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በንጋት ሐይቅ ዙሪያ የተፈጠሩትን ደሴቶች እና የቱሪዝም ፀጋዎች በመመልከት በቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

9 hours ago