(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቅዳሜ ምሽት በኒውዮርክ ወደብ 14 ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገልበጧ ምክንያት የ27 ዓመቷ ወጣት እና የአምስት ወር ህፃን ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የጀልባዋ ካፒቴን ሰዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ በማጋለጥ ወንጀል የተያዘ ሲሆን፣ ጀልባዋ ሕገ-ወጥ የኪራይ አገልግሎት እየሰጠች እንደነበር የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች (Coast Guard) እሁድ ዕለት ባወጡት መግለጫ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የኒውዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት እንደገለጸው፣ የነጻነት ሃውልት በሚገኝበት ሊበርቲ ደሴት አቅራቢያ ቅዳሜ ምሽት 4፡55 አካባቢ ጀልባ መገልበጧን የሚገልጽ ጥሪ ደርሶታል። ፖሊስ የውሃ ላይ፣ ጠላቂ እና የአየር ላይ አድን ቡድኖችን ወደ ስፍራው ያሰማራ ሲሆን፣ 12 ሰዎች ወዲያውኑ ከውሃው ውስጥ ሊድኑ ችለዋል። የሕግ አስከባሪ ምንጮች ለሲቢኤስ ኒውስ እንደገለጹት፣ ሟቾቹ የ27 ዓመቷ ሳራ ሳንቼዝ እና የአምስት ወር ህፃኗ አንቶኔላ ጋርሲያ ናቸው። ሁለቱም ተጎጂዎች ወደ ኤን.ዋይ.ዩ ላንጎን ሆስፒታል (ቢወሰዱም፣ ሆስፒታል ሲደርሱ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
አደጋው እንደተከሰተ 'ሲ ዘ ሲቲ' የተሰኘ ድርጅት ጀልባ የተገለበጠችውን ጀልባ እና ውሃ ውስጥ የገቡትን ሰዎች በማየት 11ዱን ከውሃ ውስጥ በማውጣት ለማዳን መቻሉን የድርጅቱ መስራች አዳም ሽዋርትዝ ገልጸዋል። በህይወት የተረፉት ሌሎች ተሳፋሪዎች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።
የፖሊስ ምርመራ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፣ የኒውዮርክ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኮሚሽነር እንዳረጋገጡት፣ የ46 ዓመቱ የኒውዮርክ ነዋሪ ማኑዌል ሄርናንዴዝ እሁድ ዕለት ሰዎችን ለአደጋ በማጋለጥ በ13 ክሶች ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የኒውዮርክ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አዛዥ ካፒቴን ዶሪን ማካርቲ፣ በአደጋው የሰው ህይወት በመጥፋቱ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸው፣ በነፍስ አድን ስራው ላይ የተሳተፉትን አጋር አካላት እና በጎ ፈቃደኞች ፈጣን ምላሽ አድንቀዋል። የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አክለውም፣ አንድ ጀልባ አስፈላጊውን የደህንነት መሳሪያዎች፣ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ፈቃድ እና የምርመራ ሰርተፍኬት ሳታሟላ መንገደኞችን የምታጓጉዝ ከሆነ ሕገ-ወጥ የኪራይ አገልግሎት እንደምትሰጥ ተደርጋ እንደምትቆጠር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

20 hours ago