አሜሪካ ኦሬገን እያስተናገደች ባለው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጡ።
ዛሬ ምሽት ፍጻሜውን በሚያገኘው ውድድሩ ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ ሜዳሊያ ካገኙ ደረጃቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
ከ147 ሀገራት የተወጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ባሳተፈው ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን በሴቶች በሶስት ሺ መሰናክል እና በሶስት ሺ ሜትር የሩጫ ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።
በተጨማሪም ሶስት የብር እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
35 ሃገራት ብቻ በሰንጠረዡ ውስጥ መግባት በቻሉበት ውድድሩ ኢትዮጵያ እስካሁን ስድስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአሜሪካ እና ጣልያን ቀጥሎ ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
በውድድሩ አሜሪካ በስምንት ወርቅ፣ ስድስት የብር እና አራት የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ ደረጃን ይዛለች።
ጣልያን በሶስት ወርቅ እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አምስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
DW Amharic

1 day ago