Logo
Getu Temesgen
ዲያስፋራው እና ሹምሽረት የተሰኙ ተወዳጅ ፊልሞች በቴሌቲቪ መታየት ጀመሩ!

በርካታ ድንቅ እና የተመረጡ የሀገራችንን የአማርኛ ፊልሞች ለተመልካች ሲያቀርብ የቆየው ቴሌቲቪ አሁንም በተመሳሳይ ዲያስፋራው እና ሹምሽረት የተሰኙ አዝናኛ ድንቅ ፊልሞችን በመተግበሪያው (App) ላይ ይዞላችሁ መጥቷል።

ዲያስፋራው
ተወዳጁ ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ የተወነበት ድንቅ ሥራ ነው። በተጨማሪም በበርካታ ፊልሞቿ የምናደንቃት ተዋናይት ማክዳ አፈወርቅ ከ10 ዓመታት በኋላ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪው የተመለሰችበት ፤ ታዋቂዋ ቲክቶከር ባምቢ ሀበሻ (ሐና ግደይ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራችበት እንዲሁም ተሻለ ወርቁ እና ሌሎችም ተዋንያን የተሳተፉበት አዝናኝ ፊልም ነው። በተጨማሪም በሲኒማ ቆይታውም ከ6 ወር በላይ በመታየት ሪከርድ መስበር የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው።

ሹምሽረት
በወንዶች ጉዳይና በሌሎች በርካታ ፊልሞች ተወዳጅነትን ያተረፈው ተዋናይ አድማሱ ከበደ ፈታኝና ጥሩ የታሪክ ፍሰት ያለው ስክሪፕት በማጣቱ ምክንያት ከሲኒማው ለረጅም ጊዜ ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በቅርቡ በዩልያን ተክለማርያም ተደርሶ በተዘጋጀው “ሹም ሽረት” በተሰኘው ፊልም ወደ ተመልካች ተመልሷል። በዚህ ፊልም ላይ አንጋፋዋ ተዋናይት ፍቅርተ ደሳለኝ ፣ ማስተዋል ወንደሰን እና ሌሎችም ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

የቴሊቲቪን ፊልሞችን ለመመልከት
✨መመዝገብ እና በድረ ገጽ www.teletv.et ላይ ወይም ቴሌብር ውስጥ በሚገኘው የቴሌቲቪ ሚኒ አፕ አማካኝነት ክፍያ መፈፀም ትችላላችሁ።
⚡️ከሃገር ውጪ የምትገኙ ተመልካቾችም ክፍያውን ድረገጽ ላይ በመግባት በዓለም አቀፍ ክፍያ ካርዶች መፈጸም ይችላል።

ፊልሞቹን ለመመልከት መተግበሪያውን አሁኑኑ አውርዱ https://teletv.et/download

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.