Logo
FBC
ሕገ ወጡ ህወሓት ትናንትም ለብቻው አቅም ኑሮት ስልጣን አልያዘም ፤ በሌሎች ተደግፎ እንጂ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕገ ወጡ ህወሓት ትናንት ስልጣን ሲይዝ ራሱን ችሎ አልነበረም፤ የተለያዩ ሃይሎችን ተደግፎና ከሌሎች ሀገራት ድጋፍ ተቀብሎ ነው አሉ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኦቢኤን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም÷ ሕገ ወጡ ሕወሓት ደርግን ለብቻው አሸንፎት ወደ ስልጣን አለመምጣቱን አስታውሰዋል፡፡

በወቅቱ የደርግ መንግሥት በሌሎች ጉዳዮች ተይዞ ስለነበር ያንንም እንደምቹ አጋጣሚ መጠቀሙን ነው ያስረዱት፡፡

ህወሓት ትናንትም ለብቻው አቅም ኑሮት ስልጣን አልያዘም፤ በሌሎች ተደግፎ እንጂ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ አሁን ግን እሱን መድገም አይችልም፤ ያ ዘመን አልፏል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ሕገ ወጡ ህወሓት አሁንም በድሮው መንገድ ለመሄድ በማሰብ ለመረበሽ እየሞከረ መሆኑን ጠቁመው÷ይህ አይሳካም የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታና የኢትዮጵያን አቅም ማገናዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ህወሓት በወቅቱ ይደግፉኝ የነበሩ የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ጠላቶች አሁን የሚያደርጉት ድጋፍ ከኢትዮጵያ አቅም ጋር ይጣጣማል ወይ? የሚሉና መሰል ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ ጥናቶችን ማድረግ ይገባዋል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል ምንም አይነት ተመሳሳይ ግብ የሌላቸው ሶስቱ ሸኔዎች ትብብር መፍጠራቸው እየተዳከሙ፣ አቅም እያጡና ተስፋ እየቆረጡ መምጣታቸውን እንደሚያሳይ አመልክተዋል፡፡

በዚህ እኩይ ድርጊታቸው ያልተቆጠቡት እነዚህ ሃይሎች እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ የውጭ አካላትን ለእርዳታ እየጋበዙ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

9 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.