(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቦስተን እና ቺካጎ የሚገኙ ሁለት የፌደራል ዳኞች፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከደቡብ ሱዳን እና ምያንማር (በርማ) ለመጡ ስደተኞች ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የጥበቃ ደረጃ (TPS) እና ከሀገር ያለመባረር ከለላ እንዲያቋርጥ ፈቅደዋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሰኔ ወር ከሄይቲ እና ሶሪያ ለመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ተመሳሳይ ጥበቃዎች እንዲነሱ መፍቀዱን ተከትሎ ነው። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች የተሰጠው ጊዜያዊ የጥበቃ ደረጃ እንዲቀጥል ያደረጉትን የመጨረሻ የህግ ክርክር የፌደራል ዳኞቹ ዓርብ ዕለት ውድቅ አድርገውታል።
ጊዜያዊ የጥበቃ ደረጃ (TPS) የውጭ ሀገራት ዜጎች ሀገራቸው በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች ውስጥ ስትሆን አሜሪካ ውስጥ የመሥራት ፈቃድ እና ከእስር ወይም ከማባረር ከለላ የሚሰጥ ሥርዓት ነው። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፣ የዚህ ጥበቃ መቋረጥ ወደ 232 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ዜጎችን እና 4,000 የሚደርሱ የምያንማር ስደተኞችን ከለላ ያሳጣል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ እነዚህ ስደተኞች በህግ ክርክሩ ወቅት ባገኙት "የአስተዳደር እግድ" አሜሪካ ውስጥ ሰርተው የመኖር መብት አግኝተው የነበረ ቢሆንም፣ አዲሱ የፍርድ ቤት ውሳኔ አሁንም በግጭት እና አለመረጋጋት ውስጥ ወዳሉ ሀገሮቻቸው እንዲባረሩ ክፍተት ይፈጥራል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቀዳሚ ውሳኔ፣ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ (DHS) በተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ የጥበቃ ደረጃውን ለማንሳት የሚያደርገውን ጥረት የበታች ፍርድ ቤቶች እንዳያግዱ ገድቦ ነበር። የኢሚግሬሽን ጠበቆች በመምሪያው ላይ "ይህንን መብት የማቋረጥ ስልጣን የለውም" በማለት አዲስ ክርክር ቢያነሱም፣ በቦስተን የዲስትሪክት ዳኛ ፓቲ ሳሪስ ክርክሩን ውድቅ አድርገውታል። ዳኛዋ፣ ይህን ክርክር መቀበል መምሪያው የጥበቃ ጊዜውን የማራዘም ስልጣኑን ጭምር ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው ብለዋል። በቺካጎ ዳኛ ማቲው ኬኔሊም በምያንማር ስደተኞች ላይ በተመሳሳይ ክርክሩን ውድቅ አድርገዋል።
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ (DHS) ከ2011 ጀምሮ ግጭት በማያባራባት ደቡብ ሱዳን፣ እና ከ2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ወዲህ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በገባችው ምያንማር ዜጎች ላይ የተሰጠውን ጊዜያዊ ጥበቃ ለማንሳት በህዳር 2025 እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል።
የ DHS ጠቅላይ አማካሪ ጄምስ ፐርሲቫል፣ አዲሶቹ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች መምሪያው ከወሰናቸው ውስጥ በፍርድ ቤት የታገዱት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዜጎች የጥበቃ መቋረጥ ጉዳዮችን ብቻ እንዳስቀረ ገልጸዋል። በኤክስ (X) ገጻቸው ላይም፣ "እነዚህ 'የአስተዳደራዊ እግዶች' በሚቆዩበት እያንዳንዱ ቀን፣ የአሜሪካ ህዝብ የመረጠውን እና የፈለገውን እንዳያገኝ የሚነፈግበት ቀን ነው" ሲሉ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

2 days ago