Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የመከላከያ ምርምር ላብራቶሪ መክፈቷ ተገለፀ፡፡ ሚሊተሪ ኤአይ ድረገፅ እንደዘገበው ኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የመከላከያ ምርምር ላብራቶሪን ከፍታ ስራ አስጀምራለች፡፡ እንደዘገባው ይህ ላብራቶሪ የተከፈተው በዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ድጋፍ ሲሆን አላማውም በአገሪቱ የመከላከያ ሀይልን ማዘመን ስራ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ዋነኛ ማእከል ማድረግ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኘው ይህ ላብራቶሪ ለመከላከያ ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ልማትና ልዩ ስልጠና እንደብሄራዊ ማእከል ሆኖ እንደሚያገልግልም አስረድቷል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴርን በምንጭነት የጠቀሰው ዘገባው ይህ አዲሱ ተቋም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በሳይበር ደህንነት፣ በኮሚኒኬሽን፣ በአውቶሜሽን፣ በኤሌክትሪክ ሀይል ሲስተም፣ በስሪ ዲ ህትመትና ሌሎችም ከኮምፒውተር ጋር በተያያዙ ላብራቶሪዎችን ያካተተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ላብራቶሪዎቹ ምርምርን በአነስተኛ የሰው ሀይል ስልጠና ከነባራዊው አለም አፕሊኬሽኖች ጋት በማስተሳሰር አገር በቀል ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን እድገት የማፋጠን እቅድ እንደተጣለባቸው ጨምሮ ገልጿል፡፡ ይህ ላብራቶሪ በዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ድጋፍ የተከፈተው ሁለቱ አገራት በቴክኖሎጂና ወታደራዊ መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ስምምነት ተከትሎ መሆኑን ከዘገባው ተመልክተናል፡፡

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.