Logo
SeledaPost
ኬንያ ወደ ሀገሯ ለሚገቡ የውጭ ዜጎች የጤና ኢንሹራንስ ግዴታ አደረገች

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ከኬንያ ውጭ የሚመጡ ማንኛውም ሀገር ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ከመግባታቸው በፊት ሕጋዊ የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አወጣ።

በካቢኔ ሴክሬታሪ አደን ዱአሌ በተፈረመው በዚህ ይፋዊ ሰነድ መሠረት፣ የኬንያ ዜጋ ያልሆኑ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ከ12 ወራት ላነሰ ጊዜ ወደ ኬንያ የሚገቡ የትኛውንም ሀገር ጎብኚዎችና መንገደኞች ይህ መመሪያ ይመለከታቸዋል ተብሏል።

መንገደኞች ከገዛ ሀገራቸው የገዙት የጉዞ ጤና ኢንሹራንስ በኬንያ መንግሥት የወጣውን የመድህን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ፣ በኬንያ የኤሌክትሮኒክ የጉዞ ፈቃድ (eTA) ስርዓት ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

ከጉዞ በፊት ኢንሹራንስ ያልያዙ መንገደኞች ደግሞ ኬንያ አየር መንገድ ወይም የድንበር በር ሲደርሱ በኬንያ ሕግ ከተፈቀደላቸው የኢንሹራንስ ተቋማት ገዝተው ማቅረብ ይኖርባቸዋልም ተብሏል።

የኬንያ ኢሚግሬሽን አገልግሎት የጉዞ ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት እና በሁሉም የድንበር በሮች ላይ የጤና ኢንሹራንስ ማረጋገጫውን በጥብቅ የሚቆጣጠር ሲሆን፣ ይህንን ማረጋገጫ ሳያቀርቡ ወደ ሀገሪቱ መግባት እንደማይቻል ተገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.