ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችው መስዋዕትነት ስለተከፈለላት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችው መስዋዕትነት ስለተከፈለላት ነው አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች እና ትግሎች፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እና የኦሮሞ ሕዝብ አበርክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም ኦሮሞ የኢትዮጵያ አንድ መገለጫ መሆኑን አንስተው፤ ኦሮሞ ከሌለ ኢትዮጵያ የለችም ብለዋል።
ኦሮሞ በኢትዮጵያ ምስረታ ውስጥ የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዳግማዊ ምኒሊክ ጊዜ የጦር መሪ የነበሩት ጎበና ዳጪ የኢትዮጵያን ድንበር በማስመር የነበራቸውን ሚና አስታውሰዋል።
የሚያዋጣው የተከፈለ መስዕዋትነትን ማሳነስ ሳይሆን በጉድለቱን እየሞሉ መሄድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ቅኝ ያልተገዛችው መስዋዕትነት ስለተከፈለላት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ገበየሁ ከዚህ ሄዶ ዓድዋ ላይ ተዋድቆላታል፤ ባልቻም ሰንደቋን ከፍ አድርጓል፤ የጃጋማ ኬሎ፣ የታደሰ ብሩ፣ የሀይሌ ፊዳም ሆነ የሌሎች ጀግኖች ታሪክ የሚነግረን በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ኦሮሞ ሙጫ ሆኖ ማሰባሰቡን ነው ብለዋል፡፡
በምሕረት ደምሴ

3 days ago