(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ውስጥ ሰክረው በሚያሽከረክሩ እና ህግ በሚጥሱ የውጭ ዜጎች ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንደገለጹት፣ ህግ መጣስ የቪዛ ስረዛን የሚያስከትል ሲሆን፣ ይህ ጥብቅ እርምጃ የውጭ ዜጎችን ህጋዊ ደረጃ ሊያሳጣ የሚችል ነው።
አስተዳደሩ የቪዛ ስረዛን እንደ ብሔራዊ ደህንነት ማስጠበቂያ እርምጃ አድርጎ እየተጠቀመበት ይገኛል። ቃል አቀባዩ "እያንዳንዱ የቪዛ ውሳኔ የብሔራዊ ደህንነት ውሳኔ ነው፤ ድንበር ማስከበር ደቡባዊውን ድንበር መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ማን በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር እንደሚገባ መቆጣጠርም ጭምር ነው" ብለዋል። በዚሁ መሰረት በ2025 ዓ.ም ብቻ ከ100,000 በላይ የውጭ ዜጎች ቪዛ የተሰረዘ ሲሆን፣ ይህ አሃዝ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በስልጣን በነበሩበት የመጨረሻ ዓመት ከተሰረዘው እጥፍ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
አብዛኛዎቹ ቪዛዎች የተሰረዙት ግለሰቦቹ ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በመቆየታቸው ቢሆንም፣ በርካታ ዜጎች ደግሞ በወንጀል ድርጊቶች እና ሰክሮ በማሽከርከር (DUI) ምክንያት ቪዛቸውን ተነጥቀዋል። ቶሚ ፒጎት እንዳስረዱት፣ አሜሪካ ውስጥ ቪዛ ይዘው ህግ የሚጥሱ ሰዎች የሀገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ በመሆናቸው ቪዛቸው ወዲያውኑ ይሰረዛል። ለዚህም ማሳያ ሰክረው በማሽከርከር አደጋ ያደረሱ እና በፍርድ ቤት የታዘዘ የህግ ማስከበር ፕሮግራም ላይ ሰክረው የተገኙ የውጭ ዜጎችን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባለፈው ግንቦት ወር በ'ዳካ' (DACA) ጥበቃ ስር አሜሪካ ይኖር የነበረው የ27 ዓመቱ ማይክል ሮዛሪዮ-ክሩዝ፣ በተቃራኒ አቅጣጫ ሰክሮ በማሽከርከር ባደረሰው አደጋ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 20 የሆኑ የአራት ወጣቶችን ህይወት በማጥፋቱ ክስ ተመስርቶበታል። የሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ማርክዌይን ሙሊን ይህንን አሳዛኝ ክስተት በማንሳት ግለሰቡ ከነጭራሹኑ አሜሪካ ውስጥ መግባት አልነበረበትም ያሉ ሲሆን፣ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ማስከበር (ICE) በግለሰቡ ላይ የእስር ማቆያ ትዕዛዝ አውጥቷል።
እንደ ቃል አቀባዩ ማብራሪያ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቪዛን መሰረዝ አንድን ግለሰብ ከሀገር ለማስወጣት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ቪዛው ከተሰረዘ በኋላ ግለሰቡ የሚባረረው የፍትህ ሚኒስቴር የወንጀል ክስ ሂደቱን ካጠናቀቀ ወይም የእስር ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ እንደሁኔታው ታይቶ ሊሆን ይችላል። በመጨረሻም የትራምፕ አስተዳደር ቪዛ ከተሰጠ በኋላም ቢሆን ተከታታይነት ያለው ማጣራት (continuous vetting) እንደሚያደርግ እና የአሜሪካን ህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ 'አሜሪካ ቅድሚያ' (America first) የሚለውን የቪዛ ፖሊሲ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስጠንቅቋል።

3 days ago