የኦሮሞ ሕዝብ የትግል ጥያቄዎች በለውጡ ዓመታት ምላሽ አግኝተዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ የዘመናት የትግል ጥያቄዎች ምን ያህል ምላሽ እንዳገኙ በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች አብራርተዋል።
የነፃነት ጥያቄ (አዕምሮአዊ እና አካላዊ ነፃነት)
አዕምሮአዊ ነፃነት፡ የዛሬው ትውልድ በቋንቋው ሲናገር እና ማንነቱን ሲገልጽ የሚያፍርበት እና የሚሸማቀቅበት የትላንቱ ጊዜ ማብቃቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የማይቀለበስ ነፃነት፡ የኦሮሞ ሕዝብ አካላዊም ሆነ ሥነ-ልቦናዊ ነፃነቱን መጎናጸፉን፣ ከዚህ በኋላ ሕዝቡን እንደ ቀድሞው ልግዛው፣ መሬቱን ልቀማው ወይም ልዝረፈው ብሎ ማሰብ ፍጹም "ሞኝነት" መሆኑን እና ሕዝቡ ዳግም ለባርነት የማይመችበት ከፍታ ላይ መድረሱን አስገንዝበዋል።
የዴሞክራሲ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ፡-
መቶ በመቶ ራስን ማስተዳደር፦ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ ሕግ አውጪ በመሆን፣ የቋንቋ፣ የባህል እና የማንነት መብቱን አረጋግጦ ራሱን በራሱ ማስተዳደር መጀመሩን አብራርተዋል።
ከገዳ ሥርዓት ጋር ያለው ትሥሥር፦ ይህ ራስን የማስተዳደር እና መሪን የመምረጥ ሂደት አባቶች በገዳ ሥርዓት (በአባ ቦኩ፣ አባ ዱላ እና ሲንቄ) ይጠቀሙበት የነበረውን የሥራ ክፍፍል፣ መመካከር እና የሕዝብ ተሳትፎ የሚያንጸባርቅ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን የዴሞክራሲ ሥርዓት በሂደት እየዘመነ እና እያደገ የሚሄድ ቢሆንም፣ መሠረታዊ የሆነው ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በኦሮሚያ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ምላሽ ማግኘቱን አረጋግጠዋል።
የኢኮኖሚ እና የመሬት ጥያቄ
ከሁሉ በላይ የኢኮኖሚ ጥያቄው ወሳኝ መሆኑን አንሥተው፣ በተለይም አራሹ ገበሬ ከመሬቱ ሳይፈናቀል በላቡ ሠርቶ ያገኘውን ፍሬ ራሱ የሚጠቀምበትን እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱ የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ማስፈን ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አመላክተዋል።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #currentaffairs

2 days ago