Logo
Zehabesha
የባሕር ዳሩ ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል ዛሬ ይመረቃል ::

ሁለት አመት ያህል የግንባታ ጊዜ የወሰደውና ከ40 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ የተደረገበት አዲሱ ተርሚነ‍ኣል እጅግ ዘምናዊና አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው ተብሏል::

ደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ዘመናዊ ተርሚናል የኢትዮጵያ የኤርፖርቶች ድርጅት ለማስፋፋት እቅድ ከተያዘላቸው ተርሚናሎች አንዱ የነበረ ሲሆን ግንባታዉንም በአጭር ጊዚ ውስጥ ለማጠናቀቅ ችሏል ::

በአሁኑ ሰአት በተሻለ ደረጃ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ባሟላ መልኩ የተገነባ ሲሆን በቅርቡ በአካባቢው የተመረቁ የቱርስቲ መዳረሻዎችን ጨምሮ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም የሚካሄዱ ውድድሮችን ለማስተናግድ ብሎም በዘላቂነት ለህዝቡ ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ::

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.