Logo
SeledaPost
በሸረሪና ከባድ የተኩስ ልውውጥ‼️

ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11: 45 ጀምሮ በሸረሪና አከባቢ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና እዛ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የትግራይ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ መቀስቀሱን ምንጮች ጠቁመዋል።

አርሚ 70 በመባል የሚታወቀው የትግራይ ሰራዊት አንዱ ህዋስ ይንቀሳቀስበታል ተብሎ በሚታወቀው በዚህ ስፍራ የተቀሰቀሰው ይህ ጦርነት፣ በእግረኛ እና በሜካናይዝድም ጭምር የታገዘ ከባድ (full-scale) ጦርነት መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፣ ይህ ክስተት በቅርቡ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እየተመራ ሲካሄድ የቆየውና "ጦርነት ቀስቃሽ" ይዘት ያላቸው መፈክሮች የተስተጋቡበትን ህዝባዊ ኮንፈረንስ መጠናቀቁን ተከትሎ የተቀሰቀሰ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ይሰጣሉ።
ተኩሱ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን መድፍን ጨምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እንደቀጠለ ነው፣በሽራሮ አቅጣጫ የከባድ መሳሪው ድምጽ እንደመሰማ የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል።

Seledadotio
Seledadotio
8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.