Logo
SeledaPost
በሩሲያ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ የመጸዳጃ ቤት ዉሃ የመጠጣት ውድድር ማዘጋጀቱ ዉዝግብ አስነሳ
 
በሩሲያ ስታቭሮፖል የሚገኝ አንድ የቧንቧ ሥራ ኩባንያ፣ በቅርቡ "Game of Thrones" በሚል ያልተለመደ ውድድር ምክንያት በኢንተርኔት ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊዎች አዲስ ከሆኑ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫዎች ውስጥ፣ ትላልቅ የመምጠጫ ቱቦዎችን በመጠቀም "አልኮል ያልያዘ ጋዝ ያለው መጠጥ" እንዲጠጡ ይጠበቅባቸው ነበር፤ መጠጡን በፍጥነት የጨረሰውም አሸናፊ ተብሎ ተለይቷል።
 
በስታቭሮፖል ከተማ በሚገኝ የ"ዶሚክስ" መደብር ውስጥ የተካሄደው ይህ ያልተለመደ ውድድር፣ በርካታ ተሳታፊዎች የ100,000 ሩብል (1,276 የአሜሪካ ዶላር) ሽልማት ለማግኘት ሲሉ ከመጸዳጃ ቤት ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ በፍጥነት እንዲጠጡ የሚያስገድድ ነበር። ተወዳዳሪዎቹ በሰባት ሰዎች ቡድን የተከፋፈሉ ሲሆን፣ ፈጣኑ ጠጪ ወደ ሁለተኛው ዙር ያልፍ ነበር።
 
በውድድሩ ሁለተኛ ምዕራፍ፣ ከቀዳሚው ዙር ያለፉት ሰባቱ አሸናፊዎች በተዘጋ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ በተቻለ መጠን ረጅም ጊዜ መቀመጥ ነበረባቸው፤ በመጨረሻም መቀመጥ የቻለው ሰው የዚህ ያልተለመደ ዉድድር አሸናፊ ተብሎ ታዉጇል።

በቤዛዊት አራጌ

Seledadotio
Seledadotio
17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.