Logo
YenetaTube
ከ4መቶ40 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሀምሌ 1 እስከ ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 4መቶ29.7 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 11.2 ሚሊየን ብር የወጭ፤ በድምሩ 4መቶ40.9 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል ብሏል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ቡና፣ ኤሌክትሮኒክስ፣የግንባታ እቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ጅግጅጋ እና አዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ፤ በቅደም ተከተላቸውም 1መቶ18 ሚሊየን፣1መቶ11 ሚሊየን እና 82 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 28 ተጠርጣሪዎች እና 15 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Ethio Fm

23 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.