የትናንት ስብራቶችን በምክክር የመጠገን ሀገራዊ ቁርጠኝነት
**************
በህብረ ብሔራዊ ሸማ ያጌጠች በብዝሀ አንድነት የጠነከረች እና በመደመር የደመቀችው ኢትዮጵያ የሃይማኖት የብሔር የባህል የቋንቋ እንዲሁም የሀሳብ ብዝሀነቶች መለያዎቿ ቢሆኑም ከዚህ ህብር ብዝሀነት የሚቃረኑ የነጠላ ትርክት እሳቤዎች ለዘመናት የሀገሪቱን ጉዞ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደ ኋላ እንዲሆን አድርገውታል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሳያቆሙን ታላላቅ ድሎችን ያሳካን ሲሆን ለአብነትም የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት ለውይይት ባህል መገንባት ፅኑ መሰረት ከመጣሉ ባሻገር በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉበት የሚገኘው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የትናንት ቁስላችንን የሚፈውስ የነገ እጣ ፈንታችንን የሚያፈካ እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ብቻ ሳይሆን እንደ አጠቃላይ ለሀገረ መንግስት መፅናት ትልቅ ፋይዳ የሚያበረክት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ቀርቧል።
ይህ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው ታሪካዊ የውይይት ማዕድ ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም የሆነና ሁላችንንም የሚጋብዝ የብዝሀ አብሮነት ማዕድ ነው፡፡
ይህ መድረክ የሀሳብ የበላይነትንና የድምፅ ሉዓላዊነትን በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን የውይይት ባህልን መገንባት ብርቱ ትግልን የሚጠይቅ ሂደት ቢሆንም በመንግስት ቁርጠኛ አቋም በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያልተገደበ ጥረት እና በህዝባችን ታሪካዊ አሻራ መሰረቱ በፅኑ ቆሟል።
ዘመኑን በዋጀ ተራማጅ እሳቤ እየተመራች የምትገኘው ኢትዮጵያ ከኋላቀር ተቸካይ እሳቤዎች በመላቀቅ በመደመር ፍኖተ ካርታ የበራች ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ባስመዘገበቻቸው ሁሉን አቀፍ ድሎች አፍሪካን አኩርታ ዓለምን አስደምማለች በተለይም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎችንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብለው የማይታሰቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለፍሬ ማብቃት መቻሏ ሌሎች ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዲሞክራሲያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ብሩህ ነጋችንን አፍክተዋል።
ነጠላ ትርክቶች በሀገራችን ላይ ያስከተሏቸው ስብራቶች በብሔራዊነት የወል ትርክት እየተጠገኑ ሲሆን ከፅንፈኝነት የሚነሱ የግጭት አዙሪቶችም ለሰላም በተዘረጉ እጆች እልባት ማግኘት በመጀመራቸው "እኔ ብቻ ያልኩት ካልሆነ" የሚሉ ሚዛናዊ ያልሆኑ ሀሳቦችና ትናንት ላይ ተቸክለው የቀሩ ኋላቀር አመለካከቶች በሀገራዊ የመደማመጥ እና የመከባበር እሴቶች ይገራሉ።
በፀጋዎቿ ልክ ለመበልፀግ እየታተረች የምትገኘውና በሁለንተናዊ ማንሰራራት ላይ የምትገኘው ሀገራችን የውይይት ባህልን ከመገንባት አኳያ ወደ ኋላ የማይቀለበስ ፅኑ መሰረት ያነፀች ሲሆን የትናንት ስብራቶቿን በምክክር በመቋጨት ለብሩህ ነገዋ ምቹ መደላድል ለመፍጠር ቁርጠኝነቷን አጠናክራለች።
በብሌን ደምበሎ

24 days ago