"5 ዓመት ደክሜበት ህዝብ የሚወደውን ቆንጆ ስራ ይዤ መጥቻለሁ" — ድምጻዊት ጄሪ አንተነህ
በ"ለኔ ባለው"፣ "ባዶ" እና "አላመደኝ" በተሰኙ ነጠላ ዜማዎቿ በአድማጮች ዘንድ ፍቅር ያተረፈችው ድምጻዊት ጄሪ አንተነህ፣ ለአምስት ዓመታት የለፋችበትን እና በብዙ ትጋት ያዘጋጀችውን "ወደ ንጋት" የተሰኘ ሙሉ አልበሟን ለአድማጮች አቅርባለች።
ድምጻዊቷ አልበሙን በራሷ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ለህዝብ ይፋ ስታደርግ፣ "5 ዓመት ደክሜበት ህዝብ የሚወደውን ቆንጆ ስራ ይዤ መጥቻለሁ" በማለት ስራዋ በአድማጮች ዘንድ ተቀባይነት እንደሚያገኝ ያላትን እምነት ገልጻለች።
10 ትራኮች የያዘውን ይህን አልበም ለማጠናቀቅ ከካናዳ ወደ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በመመላለስ ከፍተኛ ወጪና ጊዜ እንዳፈሰሰችበት ተናግራለች።
በአልበሙ ዝግጅትም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ታዋቂ ባለሙያዎች የሆኑት ብሩክ ተቀባ፣ ብሩክ አፍወርቅ እና ታምሩ አማረ የሰሩ ሲሆን፣ የማስተሪንግ ስራውን ደግሞ አበጋዙ ክብረወርቅ ሺዎታ እንዳከናወነ ተገልጿል።
"ወደ ንጋት" የተሰኘው አልበም ከረጅም ጊዜ ዝግጅት፣ ትጋት እና መስዋዕትነት በኋላ ለአድማጮች የደረሰ ሲሆን፣ በሙዚቃ ወዳዶች ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት እንደሚያገኝ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
ሊንኩን በመጫን ተመልከቷት
👇
https://youtube.com/jerry...

27 days ago