(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በንግድ ባንኮች ላይ ጥሎት የነበረውን ዓመታዊ የብድር ዕድገት ገደብ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ። ባንኩ ይህ እርምጃው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ አቋሙን ማላላቱን እንደማያሳይና በወለድ ተመን ላይ ወደተመሰረተ ማዕቀፍ የተደረገ "የተሳካ ሽግግር" መሆኑን በመግለጫው ቢከራከርም፣ የብድር ገደቡ በአንዴ መነሳት በገበያው ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር በማብዛት አሁን ያለውን አሳሳቢ የዋጋ ንረት ይበልጥ እንዳያባብሰው ስጋት ፈጥሯል።
ብሔራዊ ባንኩ ቀጥተኛ ያልሆኑ የፖሊሲ መሳሪያዎችን መተግበሩን እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔውን ከ15 በመቶ ወደ 16 በመቶ ከፍ ማድረጉን አስታውቋል። በተጓዳኝም ላኪዎችን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ለማርገብ በሚመስል መልኩ፣ ባንኩ የሚቆርጠውን የውጭ ምንዛሬ ኮሚሽን ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ ዝቅ አድርጓል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ላኪዎች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለብሔራዊ ባንክ በግዴታ እንዲሸጡ ተጥሎ የነበረው የ50 በመቶ ገደብ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተወስኗል።
እነዚህ ተቃራኒ የሚመስሉ እርምጃዎች (በአንድ በኩል ወለድን መጨመር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የብድር ጣሪያን ማንሳት እና የውጭ ምንዛሬ ቁጥጥርን ማላላት) ብሔራዊ ባንኩ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና አስከፊውን የውጭ ምንዛሬ ቀውስ ለመፍታት እያደረገ ያለውን መፍጨርጨር የሚያሳዩ ናቸው።
በተለይም የብድር ገደቡ መነሳት ባንኮች በነጻነት ብድር እንዲሰጡ የሚያስችል ቢሆንም፣ በ1 በመቶ ብቻ ያደገው የማሻሻያ የወለድ ምጣኔ፣ የብድር መለቀቁ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚያመጣውን የዋጋ ንረት ጫና አፍኖ ለመያዝ በቂ ነው ወይ? የሚለው የባንኩን አዲስ አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው። የላኪዎች የውጭ ምንዛሬ ገቢ ግዴታ ወደ 30 በመቶ ዝቅ መደረጉም፣ መንግስት የውጭ ምንዛሬን በቀጥታ ከመቆጣጠር ይልቅ ገበያው ራሱን እንዲያስተካክል ለማድረግ የተገደደበትን ሁኔታ ያሳያል።

26 days ago