ፉክክርና ትብብርን መርሁ ያደረገ የፖለቲካ ምህዳር
ፖለቲካዊ ፉክክር የምህዳሩን ሕያውነትና ተጠያቂነት ሲያረጋግጥ፤ ትብብር ደግሞ የሀገርን ህልውና እና መረጋጋት ይጠብቃል።
ይህንን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው።
የሰው ልጅ በውጤቱ የፉክክርም የትብብርም ፍጡር ነው።
የመደመር መንግሥት ፍልስፍም የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ባህርይ ሲተነትን በዚሁ መልክ ያቀርበዋል።
በመደመር መንግሥት ዘመን የፉክክርና የትብብርን ሚዛን ያስጠበቀ የፖለቲካ ምህዳር መገንባት ዋናው የሪፎርም ግብ ሆኖ ተቀምጧል።
የፖለቲካ ሪፎርሙ ዋና ግብም፣ አንዱን ጥሎ ሌላውን የሚያነሳ ሳይሆን ሁለቱንም መርሆዎች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ያስተናገደ ምህዳር መፍጠር ነው።
ይህ አዲስ አካሄድ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከተለመደው “አሸናፊ ሁሉንም ይወስዳል” ወይም “እኔ ከሌለሁ ሀገር ትፍረስ” ከሚል አጥፊ አስተሳሰብ በማውጣት፣ በሀሳብ ልዕልና ላይ የተመሰረተ ጤናማ ፉክክርን እና በጋራ ሀገራዊ ጥቅሞች ላይ ያተኮረ ትብብርን ማዕከል ያደረገ ነው።
የመደመር ፍልስፍና ፍጹም አንድ ወጥ አምባገነናዊ አስተሳሰብን ይቃወማል።
ይልቁንም በሃሳብ ብዝሃነት ላይ የተመሰረተ ጤናማ ፉክክርን ያበረታታል።
የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተሰራው ሥራ በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችና እስረኞች ተፈትተዋል፤ ውጪ የነበሩትም ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት በሰላማዊ መንገድ እንዲፎካከሩ ተደርጓል።
የሃሳብ ልዕልናን ለማረጋገጥ በተሰራው ሥራም ፓርቲዎች በብሔር ማንነት ላይ ብቻ ተመስርተው ከመናቆር ወጥተው፣ በአማራጭ ፖሊሲዎችና በሃሳብ ብቃት ላይ ተመስርተው እንዲፎካከሩ መንገድ ከፍቷል።
በሂደቱ እንደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነው ፉክክርን እንዲያስተናግዱ ተደርጓል።
ፉክክር ብቻውን ያለትብብር ወደ ጫካ ህግና ወደ እርስ በርስ መናቆር ሊያመራ እንደሚችል መደመር ያስገነዝባል።
ስለዚህ ፉክክር ባለበት ምህዳር ውስጥ የጋራ ትብብር የግድ ያስፈልጋል።
በዋና ዋና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ እንደ ሀገር ሉዓላዊነት፣ የህግ የበላይነት እና ታሪካዊ ስብራቶችን መጠገን ባሉ የጋራ አጀንዳዎች ላይ ፓርቲዎች በጋራ እንዲቆሙ ይጠይቃል።
የጥላቻ ፖለቲካን ለማክተም ከመገፋፋትና ካለፉት ጊዜያት አግላይ ትርክቶች በመውጣት፣ በመተባበር መንገድ አብሮ የመስራት ባህልን ያጎላል።
የጋራ ብልጽግናና ፖለቲካዊ ትብብር በቀጥታ ከኢኮኖሚና ከማህበራዊ ትስስር ጋር ተደምሮ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማምጣት እንደ ጉልበት ያገለግላል።
በመደመር መንግሥት እሳቤ ፉክክርና ትብብር ተጻራሪ ሳይሆኑ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው።
በአጠቃላይ፣ ፖለቲካዊ ፉክክር የምህዳሩን ሕያውነት፣ የሃሳብ ብዝሃነትንና ተጠያቂነትን ሲያረጋግጥ፤ ትብብር ደግሞ የሀገርን ህልውና፣ ሰላምና የጋራ ብልጽግናን ለማስቀጠል መሰረት ሆኗል።
ከመገፋፋትና ከቂም በቀል ፖለቲካ በመውጣት የሃሳብ ፉክክርን ከሀገራዊ ትብብር ጋር አጣምሮ መጓዝ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ባህልን ለመገንባት ብቸኛው አማራጭ መንገድ መሆኑን የመደመር ፍልስፍና በተግባር አሳይቷል።

27 days ago