የዓለም ባንክ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ድጋፎች የፖሊሲ ለውጦች አደረገ
የዓለም ባንክ ከ2027 እስከ 2036 ያለውን የ10 ዓመታት የአጋርነት ማዕቀፍ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት 10ዓመታት ቅድሚያ ይሰጣቸው የነበሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ ከዕቅዱ ውጪ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተው የዓለም ባንክ አዲስ የስትራቴጂ ሰነድ ትኩረቱን በዋናነት በየዓመቱ ወደ ሥራው ዓለም ለሚቀላቀሉ ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ላይ አድርጓል፡፡
ግዙፍ በመንግሥት የሚመሩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን፣ ዋና ዋና የአስፋልት መንገዶችንና የቱሪዝም ዘርፍን በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ሙሉ በሙሉ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ዝርዝር ውጪ አድርጓቸዋል፡፡
👉የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ከዕቅዱ ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባደረገችው ኢንቨስትመንት በቂ የማመንጨት አቅም ስላላት ሲሆን፣ የቱሪዝም ዘርፍ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታና የመሠረተ ልማት ሁኔታ መሻሻል እስከሚታይበት ድረስ ከዝርዝሩ ውጪ እንዲሆን መደረጉን ጠቁሟል፡፡
የከተማ አውራ ጎዳናዎችን የመገንባት ዕቅድም ቀርቶ፣ በተመሳሳይ መልኩ የገጠር መንገዶችን ወደ ማስፋፋት እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፣ ይህም አርሶአደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ለማገዝ፣ የጉምሩክ አሠራርን ለማዘመንና የወጪ ንግድ ወጪን ለመቀነስ ያለመ አዲስ መዋቅራዊ አቅጣጫ መሆኑ ተመልክቷል።
👉ባንኩ በቀጣይ እቅዶቹ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ማስተካከል፣ የኃይል መቆራረጥን መቀነስና በሚሊዮኖች ለሚቆጠር ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን አስተማማኝ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
Seledadotio

27 days ago