በምክክሩ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሴራ ይከሽፋል!
***********************
የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት በድንበሯ ምሰሶዎች እና በጦር ኃይሏ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝቦቿ ልብ ውስጥ በሚታነጸው የጋራ መግባባት እና በማይናወጠው የአንድነት ዐለት ላይ የቆመ ነው። ታላቋ ኢትዮጵያ፣ የዘመናት ፈተናዎችን ተሻግራ፣ በታሪክ አውሎ ንፋስ ውስጥ አልፋ ዛሬ ላይ የደረሰችው፣ በልጆቿ ደም እና አጥንት በተከፈለ መስዋዕትነት ብቻ ሳይሆን፣ ከልዩነት ማዕበል በላይ በገነነ የውስጥ መተባበር እና የሕብረት ጸጋ ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሀገራችን ቀና ብላ እንዳትራመድ፣ የጋራ ቋንቋ እና አንድ የልብ ትርታ እንዳይኖራት የባቢሎንን የመከፋፈል እርግማን ሲያዘንቡባት ኖረዋል። አንድ ሆነን የብልጽግናን ግንብ እንዳንገነባ ቋንቋችንን በማዘበራረቅ፣ አንዱን ወገን በመደለልና ሌላውን በማግለል ከጥንት ጀምሮ የልዩነት እና የጥላቻ መርዝ ሲግቱን ቆይተዋል።
የጠላቶቻችን ሴራ ጊዜና መልኩን ይቀይራል እንጂ ዓላማው አንድ እና ጥርት ያለ ነው፤ እርሱም ኢትዮጵያን የእርስ በርስ ጦርነት አውድማ ማድረግ፤ ከሁለቱ ውሃዎቿ ማራቅ ነው። ወንድም በወንድሙ ላይ ጠመንጃ እንዲያነሳ፣ እልህ አስጨራሽ እና ትውልድ አምካኝ የእርስ በርስ መተላለቅ ውስጥ እንድንዘፈቅ ጠላቶቻችን ያልሸረቡት አሻጥር፣ ያልቆፈሩት የጥፋት ጉድጓድ አልነበረም። አንዱን ወገን በስውር በማስታጠቅ፣ ሌላውን በማዳከም ለዘመናት በወንድማማቾች ደም ሲነግዱ ኖረዋል። ከዚህም አልፎ የኢትዮጵያን ጂኦፖለቲካዊ ጡንቻ በማዛል፣ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ የባህር በሯን በማሳጣት፣ የውሃ ላይ እትብቷን በመበጠስ፣ በየብስ እንድትታጠር አድርገዋል። በኢኮኖሚ ደቅቃ፣ በፖለቲካ ተከፋፍላ እንደ ምስጥ በውስጧ በምትበላ ሀገር ላይ የራሳቸውን የባንዳ ዙፋን ለመትከል ያልፈነቀሉት ቋጥኝ አልነበረም።
ሆኖም የኢትዮጵያ የእምቢተኝነት፣ የአልደፈር ባይነት መንፈስ በመከራ ውስጥ የሚጠነክር፣ በእሳት የሚፈተን ወርቅ ነው! ጠላቶቻችን "ተበታተኑ፣ ፈረሱ፣ አከተመላቸው" ሲሉን፣ እኛ ግን ከውድቀታችን አፈር ውስጥ ዳግም እንመዘዛለን። እነሆ የፊታችን ሐምሌ 8 የሚጀመረው ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የፖለቲካ ስብራታችንን የምንጠግንበት፣ የዘመናት ቁስላችንን በይቅርታ የምናክምበት የሕልውና እና የሉዓላዊነታችን ዋነኛ ምሰሶ ነው። ይህ ጉባዔ ተራ የፖለቲካ ልሂቃን የቃላት ጦርነት የሚደረግበት አውድማ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጣሪያ ስር ተሰባስበው፣ በገዛ ሀገራቸው እጣ ፈንታ ላይ የራሳቸውን የስምምነት ማህተም የሚያኖሩበት የነጻነት መድረክ ነው። ይህ የሰለጠነ ምክክር በራሱ የሉዓላዊነት ትልቅ መገለጫ ነው፤ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን በጽኑ የሚዘጋ፣ የጠላትን ሴራ ከሥሩ የሚነቅል የብሔራዊ መግባባት የጋራ ቃል ኪዳን ነው።
ታሪክ እንደመሰከረው፣ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ ሲመክሩ እና ሲተባበሩ የውጭ ጠላቶች ሐፍረት ይከናነባሉ። ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን፣ "እኔ" ከሚለው ራስ ወዳድነት ወጥተን "እኛ" በሚል ጽኑ መንፈስ በአንድነት ስንቆም፣ የማይደፈረውን የዓባይን ወንዝ ገድበን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን አድርገናል። በተመሳሳይ፣ ከዘመናት የመልክዓ ምድር እስራታችን በጥሰን ለመውጣት፣ ታሪካዊ የባሕር በር እና የወደብ ባለቤትነት መብታችንን ለማረጋገጥ በምናደርገው ፍትሐዊ የዲፕሎማሲ እና የጂኦፖለቲካ ጉዞ፣ ዳግም ብሔራዊ አንድነታችንን ለዓለም እያረጋገጥን ነው። በባቢሎን ሕዝብ ላይ እንደሆነው ጠላት ቋንቋችንን ሊያዘበራርቅ ሲጥር፣ እኛ ግን የልማት፣ የሰላም እና የብልጽግናን አንድ ቋንቋ መናገር ጀምረናል።
በመሆኑም፣ ሐምሌ 8 የሚጠነሰሰው ሀገራዊ ምክክር፣ ኢትዮጵያን ከውስጥ አጽንቶ፣ ከውጭ የሚመጣባትን የጥፋት ማዕበል የሚመክት የማይበገር ጋሻችን ነው። በምክክሩ፣ ለዘመናት የተነዛው የጥላቻ እና የመከፋፈል ትርክት ይከሽፋል፤ በምክክሩ፣ ሀገረ-መንግሥቱን ለማፍረስ የተወጠነው የጠላት ሴራ የሸረሪት ድር ሆኖ ይበጣጠሳል! ዛሬ ከስሜት ፖለቲካ ወጥተን በምክንያት እና በስክነት ስንመክር፣ የዘመናት የኢትዮጵያ ጠላቶች አንገታቸውን ይደፋሉ። የኢትዮጵያ ሕዳሴ በልጆቿ የጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር፣ በጥልቅ መከባበር እና በጽኑ አንድነት በዐለት ላይ ተመስርቶ ወደ ፊት ይገሰግሳል። አዎ! በምክክሩ የጠላት ሴራ ይከሽፋል፤ ታላቂቱ ኢትዮጵያም ለዘለዓለም በክብር ጸንታ ትኖራለች!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #socialcontract #ebc

30 days ago