ጀስቲን ቢበር ዓለም ዋንጫን ተቀላቀለ
#ethiopia | ፊፋ ረቡዕ ዕለት በሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳስታወቀው ታዋቂው የፖፕ ሙዚቃ ኮከብ ጀስቲን ቢበር በርካታ ከዋክብት በሚሳተፉበትና የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የዕረፍት ጊዜ የሙዚቃ ትዕይንት (halftime show) ላይ ለመሳተፍ ስሙ ተካቷል።
በዚህም መሠረት ቢበር ቀደም ሲል ዋና አጫዋች መሆናቸው ይፋ ከተደረጉት እንደ ማዶና፣ ሻኪራ እና የደቡብ ኮሪያው የሙዚቃ ቡድን ቢቲኤስ ካሉ የዓለም ታዋቂ የሙዚቃ ፈርጦች ጋር በመሆን መድረኩን በጋራ ያደምቃል።
ከተጠቀሱት ታላላቅ ከዋክብት በተጨማሪ የአፍሮቢትስ ድምፃዊ በርና ቦይ፣ ቬንዙዌላዊው የኦርኬስትራ መሪ ጉስታቮ ዱዳሜል እና በስታተን አይላንድ ኒው ዮርክ የሚገኘው የፒኤስ22 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሕፃናት የኳየር ቡድን ከታዋቂው ኮልድፕሌይ የሙዚቃ ቡድን ጋር በመሆን በመድረኩ ላይ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል።
በኮልድፕሌይ ቡድን መሪ ክሪስ ማርቲን አዘጋጅነትና መሪነት የሚቀናበረውና 11 ደቂቃዎችን ብቻ የሚወስደው ይህ የዕረፍት ጊዜ ትዕይንት፣ ከአስር ቀናት በኋላ ከኒው ዮርክ ከተማ ውጭ በሚደረገው የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ወቅት ለዕይታ ይበቃል።
ይህ ታላቅ ዝግጅት “የፊፋ ዓለም አቀፍ የዜጎች ትምህርት ፈንድ” የተሰኘውን ተቋም ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ፈንዱ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕፃናት የትምህርትና የእግር ኳስ ዕድሎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለመርዳት 100 ሚሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ አልሟል።
ጀስቲን ቢበር በሰጠው መግለጫ የዓለም ዋንጫ ሰዎችን ከማንኛውም ነገር በተለየ መንገድ አንድ የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ ታላቅ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በመሳተፉና ዝግጅቱም በዓለም ዙሪያ ላሉ ሕፃናት የትምህርት ዕድልን ለማስፋፋት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በማወቁ የተሰማውን ጥልቅ ምስጋና ገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago