"የማይሠራና ባዶ አእምሮ ለክፉና ለተንኮል አሳቦች የተመቸ ለም መሬት ነው" - ቡርኪና ፋሶ
#ethiopia | ቡርኪና ፋሶ ወጣቶችን በተለያዩ ጠቃሚ የሙያ ክህሎቶች ለማስታጠቅና የወደፊት ሕይወታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመቅረጽ ያለመ "ጠቃሚ በዓላት 2026" የተሰኘ አዲስ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምራለች።
እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ በሀገሪቱ በሚገኙ 13 ከተሞች ውስጥ በሚተገበረው በዚህ ንቅናቄ ተማሪዎች እስከ 15 የሚደርሱ ተግባራዊ የሥራ ሙያዎችን ሙሉ በሙሉ በነፃ የመማር ሰፊ ዕድል ያገኛሉ።
በሥልጠናው ከተካተቱት ዘርፎች መካከልም የቧንቧ ዝርጋታ፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና፣ የምግብ ዝግጅት፣ የፀጉር አሰራር፣ ስፌት እና የስልክ ጥገና በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ይህ ታላቅ መርሃ ግብር ወጣቶች የዕረፍት ጊዜያቸውን ያለሥራ እንዳያሳልፉ በማድረግ አእምሯቸውን በበጎ ነገር ለመጠመድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
"የማይሠራና ባዶ አእምሮ ለክፉና ለተንኮል አሳቦች የተመቸ ለም መሬት ነው" በሚለው እውነታ ላይ በመነሳት የተነደፈው ይህ ዕቅድ ወጣቶችን ለነገው ሕይወት ብቁ አድርጎ ከማዘጋጀቱም በላይ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎችም የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት ወጣቶቻቸው ላይ ትርጉም ያለው መዋዕለ ንዋይ እንዲያፈሱ ጥሪ የሚያስተላልፍ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago