Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ወዳጅ ዊንስተን ቸርችልና ተወዳጇ ውሻቸው
#ethiopia | ​የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ዊንስተን ቸርችል እና ሩፈስ የተሰኘችው ተወዳጅ ውሻቸው ታሪክ በሰው ልጅና በእንስሳት መካከል ያለውን ጥልቅ ቁርኝት የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ሆኖ በታሪክ ይነገራል።

በእንግሊዝ ታሪክ እጅግ ዝነኛ የሆነችው ውሻና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ከነበሩት ልብ የሚነኩ አጋጣሚዎች መካከል፤ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሁለቱ በአንድነት ፊልም እያዩ በነበረበት ወቅት በፊልሙ ላይ አንድ ወንጀለኛ ፖሊሶች እንዳይከታተሉት ሲል ውሻውን አንቆ በውሃ ውስጥ ሊገድለው ሲል የተፈጠረው ክስተት በዋናነት ይጠቀሳል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቸርችል ለውሻቸው ከመጨነቃቸው የተነሳ የሩፈስን አይን በእጃቸው በመሸፈን "ወዳጄ አንቺ ይህንን ማየት የለብህም፤ የሆነውን ነገር እኔ በኋላ እነግርሃለሁ" ማለታቸው ለውሻቸው የነበራቸውን ከፍተኛ ጥንቃቄ ያሳያል።

​መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ውሻ ከሰው ልጅ ጋር መጀመሪያ የተላመደ የዱር እንስሳ ሲሆን፣ በዘመናት ሂደትም የዱር እንስሳነቱ ሙሉ በሙሉ ቀርቶ የበርካታ ሰዎች ታማኝና ተወዳጅ የቤተሰብ አባል ለመሆን በቅቷል።

ይህ እንስሳቱ ለሰው ልጅ ያላቸው የወደር አልባ ታማኝነት በዘመናችንም በተለያዩ ሰዎች ዘንድ የሚመሰከር ሲሆን ውሻ ልክ እንደ ሰው የሰውን ስሜት የሚረዳ፣ በደስታና በኀዘን ጊዜ አብሮ የሚሆን እንዲሁም ባስቀየሙት ወቅት እንኳ ጥሎ የማይሸሽ የልብ ወዳጅ መሆኑ ይገለጻል።

ይህም ሁኔታ ከአንዳንድ የሰው ልጆች ይልቅ የውሻ ታማኝነትና ፍቅር እጅግ የላቀ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.