(ዘ-ሐበሻ ዜና) አዲዳስ የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያዘጋጀውን ኳስ ይፋ አደረገ፡፡ አዲዳስ ኩባንያ ለ2026 የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያ በአይነቱ ለየትና አዲስ ኳስ ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ይህ ኳስ በፍፃሜውና ለደረጃ በሚደረገው ጨዋታ ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ጠቅሶ ኳሱ ዲዛይን የተደረገው የጨዋታውን ትልቅነት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መሆኑን አስረድቷል፡፡
‹‹ትሪዮንዳ ፋይናል›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ኳስ ከአዲዳስ ባህላዊ የቀለም አቀማመጥ በተለየ ለመጀመሪያ ጊዜ ህብረ ቀለማት እንዲኖሩት መደረጉንም አስታውቋል፡፡ በኳሱ ላይ በጥቁር መደብ ወርቃማ ቀለማት ማስቀመጡን ገልፆም ይህ ውድድሩ የላቀ ሽልማት የሚያስገኝ መሆኑን እንደሚያሳይ አስረድቷል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ የኳሱ ክፍሎች ላይ ፒንክና ቀይ ቀለማትን ያስቀመጠው በሜዳ ውስጥ ተጨዋቾች ከሚያደርጉት ጫማ ጋር እንዲስማማ በማቀድ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በኳሱ ዲዛይን ጥልቅ ስፌቶችን ተጠቅሞ የሸካራነት ባህርይ እንዲኖራቸው ማድረጉንም የአየር ግፊትን ለመከላከልና የተረጋጋ ፍጥነትን ለማስፈን መሆኑን ገልጿል፡፡ ይህ ኳስ ለአለም ዋንጫ የፍፃሜ ግጥሚያዎች ከዋለ በኋላ ከጁን 7 ጀምሮ በ160 ዶላር በገበያ ላይ እንደሚውልም አስታውቋል፡፡

1 month ago