Logo
SeledaPost
ኢራን የኳታር ንብረት በሆነው ‘AL REKAYYAT’ የጋዝ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት ማድረሷ ተሰማ!

​በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ከፍተኛ ውጥረት በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት፥ የኢራን አብዮታዊ ጠባቂ ጦር  የኳታር መንግስት ንብረት በሆነውና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ በጫነው ‘AL REKAYYAT’ በተባለው ግዙፍ መርከብ ላይ የሮኬት ወይም የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሙ ተረጋግጧል።

​እንደ አክሲዮስ እና ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገባዎች ከሆነ፦ የኢራን የባህር ኃይል መርከቧ በአሜሪካ ጦር የተከፈተውን መስመር ትታ በኢራን በኩል በተመደበው መስመር እንድትጓዝ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ሆኖም መርከቧ ማስጠንቀቂያውን ችላ በማለት የአሜሪካ ባህር ኃይልን  ለእርዳታ መጥራቷን ተከትሎ ጥቃቱ ተሰንዝሮባታል።

​ መርከቧ በስተግራ በኩል  የሞተር ክፍሏ ላይ ተመትታለች። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ጭስና የእሳት አደጋ የተነሳ ሲሆን፥ የብሪታንያ የባህር ንግድ ድርጅት መርከቧ የዕርዳታ ጥሪ  ማስተላለፏን አረጋግጧል።

​ በጥቃቱ እስካሁን የሰው ህይወት አልጠፋም፤ ሁሉም የመርከቧ ሰራተኞች በሰላም ወደ ቀኝ በኩል መጽናናታቸው ተገልጿል።ኳታር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገውን የሰላም ድርድር በገለልተኝነት የምታስተናግድ ሀገር በመሆኗ፥ የኢራን አብዮታዊ ጠባቂ ይህንን ጥቃት መፈጸሙ በሁለቱ ሀገራት የሰላም ስምምነት ሂደት ላይ ትልቅ ጥያቄ እና አዲስ ቀውስ ፈጥሯል።

Seledadotio
Seledadotio

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.