የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ተሽከርካሪዎች ላይ የቴክኒክ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በክረምት ወቅት የሚከሰትን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል በተሽከርካሪዎች ላይ የቴክኒክ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
የዝናብ መጥረጊያ፣ የተሽከርካሪዎች ጎማ እንዲሁም መብራት አሟልተው እንዲገኙ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ለአሐዱ የተናገሩት በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሕዝብ ግንዛቤና የትራፊክ ሙያ ማሳደጊያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቀነኒሳ ጫካ ናቸው።
በክረምት ወቅት ለሚከሰቱ አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ችግር መሆኑንም ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል።
በክረምት የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ በከተማዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች በመንቀሳቀስ፣ እንዲሁም በመናኸሪያዎች እና በትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል።
#አሐዱ

1 month ago