Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹ከፑቲን ጋር በኮንስታንቲኖቭካ መነጋገር እፈልጋለሁ›› ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ በዶኔስክ ግዛት የሚገኘውን ኮንስታንቲኖቭካ ከተማ በተመለከተ አስተያየት ፅፈዋል፡፡

በዚህ አስተያየታቸው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ይህችን ከተማ መቆጣጠራቸውን በተመለከተ የተሰራጨውን ዘገባ ‹‹ፍፁም ውሸት ነው›› ብለውታል፡፡ ሲናገሩም ‹‹በአሜሪካ የነፃነት በአል ዋዜማ ላይ ፑቲን በጦር ግንባር ስላለው ሁኔታ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት የአለምን ህዝብና የአሜሪካን ፕሬዝደንት ለመዋሸት ወስኗል፡፡›› ብለዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹በእርግጥ በጦር ግንባር ያለው እውነታ እሱ እንደተናገረው እደለም፡፡ ይህ የተለመደ የሩሲያ ውሸት ነው፡፡ ነገር ግን ኮንስታንቲኖቭካ ከተማ እነሱ እንደሚሉት በሩሲያ ቁጥጥር ስር ከዋለ ፑቲን በዚያች ከተማ ይጥራኝና ሄጄ ጦርነቱን ማቆም በሚቻልበት መንገድ ላይ አወራዋለሁ፡፡ እውነታው ፑቲን ከሚናገረው የተለየ ቢሆንም በጦር ግንባር ያለውን ሁኔታ አይለውጠውም›› ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአንድ ቀን በፊት የሩሲያ ሚዲያዎች ፕሬዝደንት ፑቲንን እንደምንጭነት በመጥቀስ ኮንስታንቲኖቭካ በቁጥጥር ስር መዋሏን ዘግበው ነበር፡፡

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.