በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቨርቹዋል የቱሪስት መረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የውጭ መንገደኞች መውጫ ስፍራ ላይ ቨርቹዋል የቱሪስት መረጃ ማዕከል ሊገነባ ነው።
ሚኒስቴሩ ከቶፓን ኢትዮጵያ ጋር ቨርቹዋል የቱሪስት መረጃ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የጋራ መግባቢያ ሰነዱን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ እና የቶፓን ኢትዮጵያ ተወካይ ቃልኪዳን አረጋ ተፈራርመውታል።
በስምምነቱ መሰረት ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው ወጪ በሁለቱ ተቋማት የሚሸፈን ሲሆን ÷ ቶፓን ኢትዮጵያ ደግሞ ግንባታውን የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ይህ የቨርቹዋል ማዕከል በአሁኑ ወቅት እየተገነባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደሚካተት መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ከፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በኋላ አቶ ስለሺ ግርማ ከቶፓን ግሩፕ ምክትል ፕሬዚዳንት አንቶንዮ ታንጉን ጋር መክረዋል፡፡

1 month ago