(ዘ-ሐበሻ ዜና) የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ብሄራዊ ቡድኑ ከአለም ዋንጫ በመውደቁ ህዝባቸውን ይቅርታ ጠየቁ፡፡ በአለም ዋንጫ ምድብ አንድ የተደለደለችው ደቡብ ኮሪያ ቼክ ሪፐብሊክን ማሸነፍ ብችትልም በሜክሲኮና በደቡብ አፍሪካ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጭ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ይሁንና ጉዳዩ በደቡብ ከኮሪያ ውስጥ እንደቀላል አልታየም፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆንግ ሚዩንግ ቦ ይህ ውጤት መገኘቱን ተከትሎ እሁድ እለት በፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸውን ያስታወቁ ሲሆን በሜክሲኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹ውሳኔዎቼ ሁሉ ትክክለኛ ነበሩ ብዬ መናገር አልችልም፡፡ ይሁንና ለኮሪያ እግር ኳስ ይበጃል የምለውን ውሳኔ ሁሉ አሳልፌያለሁ›› ብለው ነበር፡፡
የደቡብ ኮሪያ እግር ኳስ ደጋፊዎች ግን ለተፈጠረው ውድቀት አሰልጣኙ ተጠያቂ መሆናቸውን በስፋት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ሀሳብ የአገሪቱ ፕሬዝደንት ሊ ጃይ ሚዩንግም ይጋሩታል፡፡ ፕሬዝደንቱ አሰልጣኙ ከጅምሩ እንዴትና ለምን እንደተቀጠሩ እንዲጣራም ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹በአሰልጣኙ ምርጫና በአመራር ረገድ መዋቅራዊ ጉድለቶች ያሉ ይመስለኛል›› ያሉት ፕሬዝደንቱ የባህል፣ ስፖርትና ቱሪዝም ሚኒስትር ምርመራ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጥቅሉ መንግስት የአገሪቱን ስፖርት አስተዳደር ማሻሻል እንደሚገባውም አስረድተዋል፡፡ ፕሬዝደንት ሊ ንግግራቸውን በመቀጠል ‹‹የአለም ዋንጫ ተሳትፎ ከዝግጅት አንስቶ ከፍተኛ የታክስ ከፋዮችን ገንዘብና የአገሪቱን ሀብት የሚፈጅ በመሆኑ ለደረሰው ውድቀት መንስኤዎቹ በጥልቀት ሊመረመሩና ትንተና ሊሰጥባቸው ይገባል፡፡ እንዲህ አይነት ነገሮች እንዳይደገሙም በስፖርት አስተዳደር ላይ ጠንካራ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ እንጠብቃለን›› በማለት ገልፀዋል፡፡ አክለውም ‹‹ይህ ተቀባይነት የሌለው ውጤት በመገኘቱ መላውን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ብለዋል፡፡

1 month ago