ሰው አጠፋው፤ ሰው አለማው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ፈጣሪ የሰጠንን ቀበና “ሰው “ አጠፋው ፤ ይህ የተፈጥሮ ስጦታ መጥፋት ቁጭት ያደረበት “ሰው “ ደግሞ ቀበናን ዳግም እንደ አዲስ እንዲወለድ አደረገው።
የቀበና ወንዝ ለዘመናት በዘፈን እና በትዝታ ብቻ ስሙ ሲነሳና ሲወደስ ኖሮ ዛሬ ግን ዳግም እንዲወለድ አድርገን አለማነዉ!!
አርቲስት ፀሀዬ ዮሀንስ “ቢሻን ቀበና” እያለ ብዙዎች እየዋኙ ያደጉበትን የልጅነት ትዝታን ሲቀሰቅስ፣ የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ “ቢሻን አዲስ አበባ“ እያለ ሲያደናንቅ በዘመናት ውስጥ ግን ትዝታን ብቻ ተሸክሞ የወንዙ ተፈጥሯዊ ማንነት ጠፍቶ፣ የፍሳሽ መውረጃና የቆሻሻ መጣያ ሆኖ፣ ጠረኑ አላስጠጋ ብሎ ተረስቶ የኖረ ወንዝ ነበር።
እነሆ እነዚህ የብክለት ፣ የበሽታ ምንጭና የቆሻሻ ማጠራቀሚያ የነበሩትን ወንዞቻችንን ዛሬ ላይ በትጋት እና በላብ እየታከሙ፣ ለነዋሪው ተስፋን ሀሴትን የሚለግሱ የደስታ ምንጭ እየሆኑ ነው፡፡
በአጭር ጊዜ የተገነባው ይህ ድንቅ ፕሮጀክት፣ ከሌሎች የከተማዋ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ጋር ተዳምሮ አዲስ አበባን የውበት ማማ አድርጓታል።

1 month ago