የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቋል
****************************
87.6 ሄክታር መሬት የሚሸፍነውን እና 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ዛሬ በይፋ መርቀናል።
ይህ ሰፊ መሰረተ ልማት የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎችን በጋራ የያዘ ነው።
ፕሮጀክቱ የግንባታ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ መዲናችንን የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋምና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች፣ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስልታዊ ሽግግር የሚያፋጥን ታላቅ አጋጣሚ ነው።
የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን
1 month ago