ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ 32ቱን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ 32ቱን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።
በምድብ-11 የመጨረሻ ጨዋታ ኡዝቤክስታንን የገጠመችው አፍሪካዊቷ ሀገር ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ በ4 ነጥብ ከምድቧ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀች ሲሆን፥ ምርጥ 3ኛ በመሆን የ32ቱን ጥሎ ማለፍ ተቀላቅላለች።
በዚሁ ምድብ ፖርቹጋል ከኮሎምቢያ ያደረጉት የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኮሎምቢያ ምድቡን በበላይነት ያጠናቀቀች ሲሆን፥ ፖርቹጋል 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች።
በምድብ-12 በተደረገ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ክሮሺያ ጋናን 2 ለ 1 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።
በዚሁ ምድብ እንግሊዝ ፓናማን 2 ለ ዐ አሸንፋለች።

1 month ago