Logo
Getu Temesgen
ጠራ ሲባል እየደፈረሰ
#ethiopia | የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሆርሙዝ ሰርጥና በሌሎች ወሳኝ ቀጠናዎች ላይ “ከባድ የአየር ጥቃት” መፈጸሙን ይፋ አደረገ። ይህ የአሜሪካ እርምጃ የተወሰደው ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ በንግድ መርከብ ላይ የአራት ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ የተሰጠ አፀፋዊ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል።

ፎክስ ኒውስ ዋሽንግተንን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ ስድስት የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሆርሙዝ ዳርቻዎች በገሽም ደሴት እንዲሁም በሲሪክ አካባቢዎች የሚገኙ አራት ወሳኝ የራዳር እና የሚሳዔል ስርዓት ዒላማዎችን የመታች ሲሆን በቦታዎቹ ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱንም የኢራን ሚዲያዎች እያረጋገጡ ይገኛሉ።

​ከዚህ ጥቃት አስቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ገጻቸው ላይ ኢራን በንግድ መርከቦች ላይ ለምትሰነዝረው ትንኮሳ ምላሽ እንደሚሰጥ አስታውቀው የነበረ ሲሆን ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው ኢራን የፈረመችውን የሰላም ስምምነት እንደሚያከብሩ ገልጸው “ጥቃትን ግን በጥቃት እንመልሳለን” በማለት የዋሽንግተንን ጽኑ አቋም አንጸባርቀዋል። በሌላ በኩል፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል (IRGC) የአሜሪካን ጥቃት አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን፣ ዋሽንግተን ሁልጊዜም ቃሏን ታጥፋለች በሚል በመክሰስ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካን ዒላማዎች መምታቱን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ዜናው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በጥቃቱ የደረሰው ትክክለኛ የጉዳት መጠንና የኢራን አጸፋዊ ምላሽ ዝርዝር መረጃ በይፋ አልተጋራም።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.