(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፊፋ ሩሲያ ወደአለም ዋንጫ እንድትመለስ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰማ፡፡ የአለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ የሆነው ፊፋ ሩሲያን ወደአለም ዋንጫ ውድድሮች የሚመልስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ይህን ውሳኔውንም ለአዘርባጃን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
አዘርባጃን የመጀመሪያውን የወጣቶች ማለትም እድሜያቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን አለም ዋንጫ የምታስተናግድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ውድድር የፊታችን ኦክቶበር 22 ቀን 2026 ተጀምሮ ኦክቶበር 31 የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
ፊፋ ለአስተናጋጇ አገር በፃፈው ደብዳቤ ላይ ‹‹ሁሉም የፊፋ አባል አገራት በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላሉ›› የሚል መመሪያ አስተላልፏል፡፡ ይህ ማለት ሩሲያም የፊፋ አባል በመሆኗ በውድድሩ ላይ እንድትሳተፍ ፈቃድ ማግኘቷን የሚገልፅ ነው፡፡
የዩክሬይንና ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ፊፋ በሚያደርጋቸው ማናቸውም ውድድሮች ላይ ሩሲያ እንዳትሳተፍ ገደብ የጣለ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ግን በመጪው ጥቅምት ወር በሚከናወነው በዚህ የመጀመሪያው ከ15 አመት በታች የአለም ዋንጫ ላይ ሩሲያ ወደውድድሩ እንድትመለስ ፈቅዷል፡፡ ይህ ውድድር በ2027 በሴቶች የሚደረግ ሲሆን ከ2028 አንስቶ የሴቶችና የወንዶች የታዳጊዎች አለም ዋንጫ በእኩል ጊዜ እንደሚደረግ ፊፋ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

2 months ago