(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) በደቡብ ኮሪያ መዲና ሴኡል፣ ዮኢዶ በሚገኘው የብሔራዊ ምክር ቤት አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 17 (ጁን 24) ዕለት 34 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች መድረኩን ሲቆጣጠሩት አዳራሹ በልዩ ስሜት ተሞልቶ ነበር። አምስት እና ስድስት እየሆኑ በመከፋፈል መድረክ ላይ የወጡት እነዚህ ታዳጊዎች፣ የደቡብ ኮሪያን ብሔራዊ መዝሙር እና ታዋቂውን መንፈሳዊ ዜማ ‘አሜዚንግ ግሬስ’ አቅርበዋል። በመጨረሻም 34ቱም በአንድነት በመሆን ‘ሆሎ አሪራንግ’ እና ‘አመሰግናለሁ፣ እወዳችኋለሁ’ የተሰኙትን የኮሪያ ዜማዎች ሲያዜሙ፣ ከ500 በላይ የሚሆኑት የአዳራሹ ታዳሚያን ከመቀመጫቸው በመነሳት በሞቀ ጭብጨባ አክብሮታቸውን ገልጸውላቸዋል።
እነዚህ አስደናቂ ታዳጊዎች ‘የቃኘው መዘምራን’ አባላት ናቸው። መዘምራኑ ከ1950 እስከ 1953 በተካሄደው የኮሪያ ጦርነት ወቅት ደቡብ ኮሪያን ለመርዳት የዘመቱት የጀግናው የኢትዮጵያ ‘ቃኘው ሻለቃ’ አባላት የልጅ ልጆች ናቸው። የቃኘው ሻለቃ በጦርነቱ ከተሳተፉት የውጭ ኃይሎች ብቸኛው አፍሪካዊ ጦር ሲሆን፣ በተሳተፈባቸው 253 ውጊያዎች በሙሉ አንዴም ሳይሸነፍ 253 ጊዜም ድል በማድረግ አስገራሚ ታሪክ የጻፈ ነው።
ኢትዮጵያውያኑ የጦርነት ተሳታፊዎች በኮሪያ ጦርነት ያደረጉትን ተጋድሎ 75ኛ ዓመት መታሰቢያ፣ እንዲሁም የአርበኞች ድጋፍ ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ‘የኮሪያ ጦርነት ተሳታፊ ሀገራት መታሰቢያ ማህበር’ እና ‘ዋርም ዋን ዴይ ፋውንዴሽን’ የተባሉ ተቋማት የቃኘው ሻለቃ አርበኞች የልጅ ልጆችን ዘንድሮ ወደ ኮሪያ ጋብዘዋቸዋል።
ከ8 እስከ 16 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትን 34ቱን የመዘምራን አባላት፣ የ95 ዓመቱን አንጋፋ የቃኘው ሻለቃ አርበኛ አቶ ተስፋዬ አስማማውን፣ አዘጋጆችን እና አስተባባሪዎችን ጨምሮ በድምሩ 41 ሰዎችን የያዘው የኢትዮጵያ ልዑክ፣ ሰኔ 15 (ጁን 22) ነበር የኮሪያን ምድር የረገጠው።
የ14 ዓመቱ የመዘምራኑ አባል አልዓዛር ሙሉጌታ፣ "ድካም እስኪጠፋኝ ድረስ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ስራችንን ያለምንም ስህተት አቅርበን ከጨረስን በኋላ ሴኡል ከተማን መጎብኘት እፈልጋለሁ" ሲል ስሜቱን ገልጿል።
ከቀድሞው የኢትዮጵያ ክቡር ዘበኛ ተውጣጥተው የነበሩት በርካታ የቃኘው ሻለቃ አርበኞች፣ በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው የደርግ ስርዓት ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለእስራት፣ ለመገለል እና ለከፍተኛ ድህነት ተዳርገው ነበር። ‘ዋርም ዋን ዴይ ፋውንዴሽን’ ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ አርበኞቹን እና ቤተሰቦቻቸውን መደገፍ የጀመረ ሲሆን፣ ይሄው ‘የቃኘው ኮዋየር’ በልጅ ልጆቹ አነሳሽነት በ2018 ተመስርቷል።
የመዘምራኑ አባላት ለዚህ ዝግጅት ፈታኝ ሁኔታዎችን አልፈዋል። የ16 ዓመቱ ስምዖን ታምራት የተጋፈጡትን ፈተና ሲያስታውስ "ወደ ልምምድ ቦታ ለመድረስ በባስ 5 ሰዓታት እንጓዝ ነበር፤ ለ8 ወራት ሙሉ ተለማምደናል። በአንድ ወቅት ማታ ከልምምድ ስመለስ በዘራፊዎች ተጠቅቼ ጉዳት ደርሶብኝ ነበር፤ ግን አሁንም ልምምዴን አላቋረጥኩም።" ብሏል። አክሎም "አያቴ በወጣትነቱ የተዋደቀላትን ሀገር መጎብኘት ትልቅ ትርጉም አለው። አያቴ ወደ ኮሪያ ስሄድ በቹንቾን የኮሪያ ጦርነት አርበኞች መታሰቢያ ስፍራ ላይ አበባ እንዳኖር አደራ ብሎኛል" ሲል ተናግሯል።
መዘምራኑ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መንግስት በተዘጋጁ ብሔራዊ መታሰቢያ ዝግጅቶች ላይ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ከሀገር ውጪ ሲጓዙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ትናንት ሰኔ 16 (ጁን 23) የደቡብ ኮሪያ ነጻነት ታጋዮች የልጅ ልጆች ከሆኑት ‘ሂሮ ሃናሊም ኮዋየር’ ጋር ሴኡል በሚገኝ ስቱዲዮ በመገናኘት ‘You Raise Me Up’ የተሰኘውን ታዋቂ ዜማ በአንድነት ዘምረዋል።
የቃኘው ኮዋየር አባላት ነገ ጁን 25 በጃምሲል ቤዝቦል ስታዲየም በሚካሄድ የባለሙያዎች የቤዝቦል ጨዋታ ላይ የብሔራዊ መዝሙር ያቀርባሉ። ከዚያም በሴኡል፣ ቹንቾን፣ ዴጆን፣ ሱዎን እና ቡሳን በሚገኙ ዋና ዋና አብያተ ክርስቲያናት እና ወታደራዊ ተቋማት ጉብኝት የሚያደርጉ ይሆናል። ሐምሌ 21 (ጁላይ 28) ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊትም በሁለቱ ኮሪያዎች ድንበር ጉብኝት ማድረጉን እና የቴኳንዶ ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ የኮሪያ ባህሎችን ይለማመዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

2 months ago