የትኛውም ትውልድ የሀገር ግንባታን ብቻውን ስለማያጠናቅቅ፣ ሁላችንም መሠረቱን የማጠናከር የጋራ አደራ አለብን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ሀገር መገንባትን መንግሥት፣ ገበያውም ሆነ ማኅበረሰቡ ለብቻቸው ሊወጡት ስለማይችሉ ሁሉም በጋራ ሊረባረብ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያ ታከናውናለች" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው መድረክ ላይ እንዳብራሩት፣ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ትውልድ በተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ ብቁ ሆኖ እንዲያድግ እና እንዲበለጽግ ማዘጋጀት እጅግ ወሳኝ ነው።
ለዚህም ጥራት ያለው ትምህርት እና የሥራ ዕድሎች በሰፊው መገኘታቸውን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም የምንገነባቸው ተቋማት የትውልዱን አቅም በሚገባ አልምተው የሚያወጡ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሀገር ግንባታ ሂደት የሁሉንም አካላት ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "የጀመርናቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እውነተኛ ስኬት የሚለካው በሚያመጡት ተጨባጭ ውጤት" ነው ብለዋል።
ሪፎርሞቹ ተወዳዳሪ የሆኑ ኩባንያዎችን መፍጠር መቻላቸውን፣ በቂ የሥራ ዕድል መክፈታቸውን እንዲሁም ለሁሉም ማኅበረሰቦች እና ትውልዶች የሚተርፍ ዘላቂ ብልጽግናን ማምጣት መቻላቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ የሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞው ስኬታማ መሆን አለመሆኑን እንደሚያመላክት አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ ይህን የለውጥ ምዕራፍ በራስ መተማመን እና በግልጽነት እንደምትጋፈጠው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሀገራችን በጋራ መከባበር ላይ የተመሠረተ ውይይትን እንዲሁም በላቀ ጥበብ እና በጋራ ዓላማ ወደፊት ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን እንደምትፈልግ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት መላው ዓለም የኢትዮጵያን ትራንስፎርሜሽን ከፊሉ በማበረታታት፣ ከፊሉ ደግሞ በጥርጣሬ እየተከታተለው መሆኑን አንስተዋል።
የመንግሥት ግልጽ ግዴታ ግን የሕዝብን ፍላጎት እና ምኞት ማገልገል፣ ዕድሎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሰፊው ማዳረስ፣ እንዲሁም ጠንካራ፣ ፍትሐዊ እና ዘላቂ ተቋማትን መገንባት ስለመሆኑ በአፅንዖት ተናግረዋል።
የትኛውም ትውልድ የሀገር ግንባታ ሥራን ብቻውን ፈጽሞ እንደማያጠናቅቅ በማንሳት እያንዳንዱ ትውልድ ጠቃሚ የሆኑ እሴቶችን የመጠበቅ፣ ስህተቶችን የማረም እና ቀጣዩ ትውልድ የሚገነባበትን መሠረት የማጠናከር የጋራ አደራና ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ይህ ታላቅ ሥራ "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" እንደሚባል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እርሱም ሀገራችን ወደፊት የምታሳካው ታላቅ የመመንጠቅ ዕድገት መጀመሪያ መሆኑን አብራርተዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #nationbuilding #sharedresponsibility #ethiopiadelivers #ebc

2 months ago