Logo
YenetaTube
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት 24 ቦታዎች ላይ የቅርስ ጥገና መደረጉ ተገለፀ

በፈረንሳይ መንግስት የተጀመረው የላሊበላ ፕሮጀክት በውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ የተለዩ 24 ቦታዎች አስቸኳይ ጥገና እንደተደረገላቸው የላሊበላ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዲያቆን አድሴ ደምሴ ተናግረዋል።

ለጥገናው ሥራ የፀጥታ ችግር እንቅፋት አለመሆኑን አንስተው ውስጡን የማስዋብ፣ መሰረተ ልማቶችን የማሟላትና ለጎብኚዎች ሳቢ ማድረግ እንደተቻለም ገልፀዋል።

ሌሎች ጥገና የሚያስፈልጋቸው ቅርሶች መኖራቸውን ገልፀው፣ በፈረንሳይ መንግስት የተጀመረው ዘላቂ የላሊበላ ፕሮጀክት ከሶስት ዓመት በላይ የፈጀ ነው ብለዋል።

በአካባቢው ዘላቂ ልማት እንዲኖር ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶት ፕሮጀክቱ እንዲቀጥል ተደርጓል ሲሉም አስታውቀዋል።

ዘላቂ የላሊበላ ፕሮጀክት (Sustainable Lalibela Project) በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መንግስታት ስምምነት የተጀመረ፣ የዓለም ቅርስ የሆነውን የቅዱስ ላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለመጠገን የታቀደ መሆኑንም ገልፀዋል።
#አሐዱ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.