Logo
Getu Temesgen
ቄራ ላይ ታላቅ ሕዝባዊ የእግር ክኳስ ክለብ ተቋቋመ!
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ካስ ታሪክ ውስጥ አንጋፋና ታላቅ ስም ያለው የቄራ አንበሳ ክለብ ዳግም ተቋቁሟል። ይህ ክለብ መሠረቱ በታላቋ ቄራ አልማዝዬ ሜዳ ሲሆን ከሃምሳ ስምንት አመት በኋላ ተጠናክሮ መጥቷል።

ባሳለፍነው እሁድ ከአንድ ሺህ በላይ የቄራና አካባቢው ነዎሪዎች በተለይም ቡድኑ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጋር ተስተካካይ ዕድሜ ላይ እንደመገኘቱ በዚህ መልክ ወደኋላ መቅረቱ ቁጭት የፈጠረባቸው በምሥረታ ጉባኤ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል።

አልማዝዬ ሜዳ ያፈራቻቸው ለብሔራዊና ለክለብ የተጫወቱ በርካታ ተጫዋቾች እጅ ለእጅ በመያያዝ ለክለቡ ድጋፍ ለማድረግ በዕለቱ ቃል ገብተዋል።

የቄራ አንበሳ ቀደም ሲል ፕሪሚየር ሊግ ለመግባት ጫፍ የደረሰ ቢሆንም በፋይናንስ ችግር ከውድድር ርቆ ለመቆየት ተገዷል።

አሁን ግን በአካባቢው ባለሀብቶች እየታገዘ ጥሩ ደረጃ ላይ ሲገኝ የአልማዝዬ የታዳጊ ፕሮጄክት አንዱ ማሳዬ ነው።
" ቄራ ተወልዳችሁ በእግር ኳስ ያለፋችሁ አካባቢያችሁን አልፋችሁ ውበት የለም። ስለሆነም ቄራ ታስገድዳችሁለች" በሚል ለብሄራዊ እና ክለብ ተጫዋች ለሆኑ የአልማዝዬ ሜዳ ፈርጦች ትልቅ የቤት ሥራ ተሰጥቶአቸዋል።

አልማዝዬ ሜዳ በዚህ መልኩ ዘመናዊ ሆኖ ለቄራ ማሕበረስብ እንዲያገለግል ያደረጉት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቢቤ በጉባኤው ተመስግነዋል።

https://youtu.be/ytB-gccE6...

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.