Logo
Getu Temesgen
የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከኢራን ጋር በተደረሰው የኒውክሌር ስምምነት ዙሪያ ተግባራዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ
#ethiopia | የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በተመለከተ ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመሻገር ዝግጁ መሆናቸውን በይፋ ገልጸዋል።

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በፈረመችው አዲስ የመግባቢያ ሰነድ አማካኝነት የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ላለማምረትም ሆነ በባለቤትነት ላለመያዝ ዳግም ቁርጠኝነቷን አረጋግጣለች።

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ አገራት ኢራን አከማችታው በሚገኘው የበለጸገ ዩራኒየም ጉዳይ ላይ በጋራ ለመወያየት ተስማምተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ራፋኤል ግሮሲ ዛሬ ማለዳ በሰጡት መግለጫ ሊያጋጥሙ በሚችሉ የቴክኒክ ፈተናዎች ላይ ብቻ በማተኮር ጊዜን ማባከን ተገቢ እንዳልሆነ አሳስበዋል።

ሁሉም ወገኖች በቅን ልቦና ተሳትፎ በማድረግ ስምምነቱ ግቡን እንዲመታ ይፈልጋሉ በሚል እምነት ድርድሩን እንደሚመሩት የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ስምምነቱን መፈረማቸው ራሱ ሂደቱን በቁም ነገር ለመተግበር ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳይ ምልክት መሆኑን ጠቁመዋል።

ኤጀንሲው ስለ ተወሰኑ ጉዳዮችና ፍተሻ ሊደረግባቸው ስለሚገቡ ስፍራዎች በቂና አስተማማኝ መረጃ እንዳለው የጠቀሱት ግሮሲ፣ ሆኖም ከሂደቱ ቀድሞ መደምደሚያ ላይ መድረስ ትክክል እንዳልሆነና በአሁኑ ወቅት በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል።
#iran #nuclear #iaea #rafaelgrossi #worldnews #internationalrelations #usa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

21 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.