የጀርመን ጦር መርከቦች ወደ ቀይ ባህር እየገሰገሱ ነው
#ethiopia | ጀርመን በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ወታደራዊ ተልዕኮ ቅድመ-ዝግጅት ለማድረግ ሁለት የጦር መርከቦችን ወደ ቀይ ባህር እያሰማራች መሆኑን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቦሪስ ፒስቶሪየስ ዛሬ ሐሙስ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ በብራስልስ ከኔቶ አቻዎቻቸው ጋር ለሚያደርጉት ስብሰባ በደረሱበት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ “በአሁኑ ሰዓት ‘ፉልዳ’ የተሰኝች ፈንጂ አላሚ መርከባችን እና ‘ሞዘል’ የተሰኘችው ሌላኛዋ መርከብ በሱዌዝ ቦይ በኩል ወደ ቀይ ባህር በመጓዝ ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።
ሆኖም ቦሪስ ፒስቶሪየስ አክለው እንዳብራሩት፤ ጀርመን በማንኛውም ፈንጂ የማፅዳት ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ከኢራን እና ከኦማን ቅድመ ፈቃድ ማግኘት የሚኖርባት ሲሆን፣ አጠቃላይ ተልዕኮውም በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በሚደረጉት ቀጣይ ንግግሮች ሂደትና ለውጦች ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ማን ያጠመደውን ፈንጂ እንደሚያመክኑ ከማንስ ጋር ጦር እንደሚገጥሙ ያሉት ነገር ባይኖርም ፖለቲከኞች ጉዳዩ የየመኑን አማፂ የሚመለከት ሳይሆን አይቀርም ብለዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago