የአማራ ወጣቶች እንዲታገሉ አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ‼️
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ ለአማራ ወጣቶች የትግል ጥሪ አቀረቡ፡፡ ‹‹አመራሮቹን ሄዳችሁ ታገሏቸው›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አረጋ ይህን ያሉት “ባህር ዳርን ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና የማይተካ ነው” በሚሉ መሪ ቃላት ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።
ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቾት አልባ የሚያደርገው የአስተዳደር ብልሽት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ አመራሩ በቀላሉ የሚገኝ፣ ቀላልና ውሳኔ መስጠት የሚችል መሆን እንዳለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በተለይም በሕዝብና በሀገር ላይ የሚፈጸሙ የሌብነት ድርጊቶችን ወጣቱ በግንባር ቀደምትነት ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል።
“ሌብነት ውስጥ የመሬት ስርቆት፣ የግብር ስርቆት፣ የኮንትራት ስርቆት ውስጥ የሚገባ፣ ግን መስረቅ ሳያንስ የሚመራውን ደሃ ሕዝብ የጎሪጥ የሚያይ አመራር ላይ በጽናት መታገል ያስፈልጋል።” ሲሉ የባህር ዳር ወጣቶች በተሰበሰቡበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
Seledadotio

2 months ago