Logo
Getu Temesgen
ጋዜጠኛ ያልተቀጠረለት ምስጥራዊው የሩሲያ የሬዲዮ ጣቢያ

​#ethiopia | ሸገር የሬዲዮ ጣቢያን ካለ ዜና አልያ ካለ ፕሮግራም እና ሙዚቃ ውጭ እስቲ አስቡት? በዓለም ዙሪያ ያሉ የሬዲዮ መገናኛ አጥኚዎችን እና ተመራማሪዎችን ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያወዛግብ የቆየውና "ዘ ቡዘር" በመባል የሚታወቀው ምስጢራዊው የሩሲያ አጭር ሞገድ ሬዲዮ ጣቢያ "ዩቪቢ-76" ፣ አሁንም ድረስ ትክክለኛ አላማው ሳይታወቅ ስርጭቱን እንደቀጠለ ነው።

​በ4625 ኪሎ ኸርዝ (kHz) ሞገድ ላይ የሚሰራጨው ይህ ጣቢያ፣ በቀን ለ24 ሰዓታት አሰልቺ እና ተደጋጋሚ የሆነ የ"ቡዝ" ድምጽ ያሰማል። ጣቢያው ስርጭቱን ከጀመረበት ከ1970ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ድምፁ ድንገት ተቋርጦ በሩሲያኛ ቋንቋ ቁጥሮችን፣ ስሞችን እና አጫጭር መልእክቶችን የሚያነቡ ሰዎች ድምፅ ይሰማል። ሆኖም ግን የመልእክቶቹ ትርጉምም ሆነ የጣቢያው ትክክለኛ አገልግሎት እስካሁን በውል አልታወቀም።

​ስለ ጣቢያው ምንነት እና አላማ ከተለያዩ አካላት በርካታ መላምቶች ያሉ ሲሆን
​በርካቶች ጣቢያው በዓለም ዙሪያ ለተሰማሩ የሩሲያ ሰላዮች ምስጢራዊ መልእክቶችን ለማስተላለፍ እና ለሩሲያ ጦር ሰራዊት በተለይም ለምዕራባዊው ወታደራዊ እዝ እና ለተለያዩ የጦር ሰፈሮች መገናኛነት እንደሚያገለግል በስፋት ይገመታል።

​አንዳንዶች ደግሞ ይህ ጣቢያ ሩሲያ የኒውክሌር ጥቃት ቢሰነዘርባት እና ከፍተኛ አመራሮቿ ቢገደሉ፣ በራስ ሰር የኒውክሌር አፀፋዊ ጥቃት እንዲሰነዘር የሚያደርገው ስርዓት አካል ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።

​ምንም እንኳን ጣቢያው ከቦታ ቦታ ከሞስኮ አቅራቢያ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ አካባቢ መቀየሩ ቢታወቅም፣ የሩሲያ መንግስት ስለ ጣቢያው ህልውናም ሆነ አላማ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ የለም። በዘመናዊው የዲጂታል ኮሙኒኬሽን እና የሳተላይት መገናኛ ዘመን፣ ይህ አሮጌ የአጭር ሞገድ ሬዲዮ ጣቢያ ያለማቋረጥ ስርጭቱን መቀጠሉ አሁንም ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንቆቅልሽን እንደሆነ ቀጥሏል ቀጥሏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.