(ዘ-ሐበሻ ዜና) አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን አገራዊ የምክክር ጉባዔ ከቀጣዩ ሐምሌ 8 ጀምሮ በአዲስ አበባው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እንደሚያካሂድ አስታውቋል። አራት ሺሕ ገደማ ጉባኤተኞች ይሳተፉበታል የተባለውና ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው ይህ ታሪካዊ ጉባዔ፣ አገሪቱን ለዘመናት ሲያተራምሱ በቆዩ እና እጅግ ስሱ በሆኑ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ላይ የመጨረሻውን ምክክር እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በዚህ አገር አቀፍ መድረክ ላይ ውሳኔ እና የጋራ መግባባት ይደረግባቸዋል ተብለው ከተያዙት አጀንዳዎች ክብደት አንጻር፣ ጉባዔው የኢትዮጵያን የፖለቲካ መሰረት ሊያናውጡ ወይም ሊያስተካክሉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያል። የሕገመንግሥት ማሻሻያ፣ ለዘመናት ምላሽ ያላገኙ የማንነት ጥያቄዎች፣ የክልሎች የድንበር አከላለል ውዝግቦች፣ የፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጉዳይ፣ እንዲሁም ከብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ጋር ተያይዞ ያለው የሰላ የፖለቲካ ልዩነት የጉባዔው ዋነኛ የትኩረት ነጥቦች ናቸው። ይሁን እንጂ እነዚህን መሰረታዊ እና ለጦርነት ሳይቀር ምክንያት የሆኑ ጥልቅ የፖለቲካ ልዩነቶችን በ15 ቀናት ጉባዔ ብቻ እልባት መስጠት ይቻላል ወይ? የሚለው ጉዳይ በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ክሪቲካል ጥያቄ ሆኖ ብቅ ብሏል።
ኮሚሽኑ እስካሁን ባደረገው የምክክር ሂደት 1 ሺሕ 234 የአገሪቱን ወረዳዎች ያሳተፈ መሆኑን እና በአጠቃላይ 93 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን ክፍል መሸፈኑን እንደ ትልቅ ስኬት አንስቷል። ይህ አሃዛዊ መረጃ የኮሚሽኑን ሰፊ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ቢሆንም፣ የትግራይ ክልል በዚህ አገር አቀፍ የምክክር ሂደት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አለመሳተፉ የሂደቱን "አገራዊነት" እና አሳታፊነት በጽኑ የሚፈታተን ትልቅ ክፍተት ነው።
በትግራይ ክልል ምንም አይነት የምክክር ሂደት አለመካሄዱ እና የክልሉ የፖለቲካ ኃይሎችም ሆኑ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በጉባዔው አለመሳተፋቸው፣ በተለይም እንደ ሕገመንግሥት ማሻሻያ እና የድንበር አከላለል ባሉ አጀንዳዎች ላይ የሚደረገውን ብሔራዊ መግባባት ጎዶሎ ያደርገዋል። አገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከገባችበት ጥልቅ የፖለቲካ እና የጸጥታ አዘቅት ለመውጣት በሚደረገው በዚህ ወሳኝ ጉባዔ ላይ፣ የትግራይ ድምጽ አለመካተቱ በቀጣይ አገራዊ ዕርቅ እና የፖለቲካ መረጋጋት ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ላይ የራሱን አሉታዊ ጥላ ማጥላቱ አይቀርም።
ይህ ጉባዔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አቅጣጫ ለመቀየር ወሳኝ እርምጃ ተደርጎ ቢወሰድም፣ የሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም የትግራይ አለመሳተፍ፣ እንዲሁም የአጀንዳዎቹ እጅግ ውስብስብነት፣ የኮሚሽኑን የመጨረሻ ግብ ስኬት በፈተና ውስጥ የሚጥለው መሆኑ አያጠራጥርም።

2 months ago