Logo
Getu Temesgen
የዶናልድ ትራምፕን ስም ከማዕከሉ ሊወገድ መሆኑ ተሰማ
#ethiopia | ​ታዋቂው የኪነ ጥበብ ማዕከል የሆነው ‹ኬኔዲ ማዕከል› በፍርድ ቤት በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ስም ከህንፃው የውስጥና የውጭ ክፍሎች እንዲሁም ከድረ-ገጹ ላይ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አንድ የማዕከሉ ባለስልጣን አረጋገጡ።

​የህንፃ ግንባታ ሠራተኞች ቅዳሜ ዕለት በማለዳ የፕሬዚዳንቱን ስም ከህንፃው የፊት ለፊት ገጽታ ላይ የማንሳት ስራቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ ብይን የሰጡ አንድ ዳኛ በፕሬዚዳንቱ የተመረጡት የማዕከሉ የቦርድ አባላት የዚህን ታሪካዊ ማዕከል ስም የመቀየር ህጋዊ ስልጣን እንደሌላቸው መወሰናቸው ይታወሳል። የዩናይትድ ስቴትስ አውራጃ ዳኛ የሆኑት ክሪስቶፈር ኩፐር ባለፈው ግንቦት 29 ባወጡት የጽሁፍ ውሳኔ፣ "ለኬኔዲ ማዕከል ስሙን የሰጠው ኮንግረስ በመሆኑ፣ ስሙን መቀየር የሚችለውም ኮንግረስ ብቻ ነው" ሲሉ አስገንዝበዋል።

​ማዕከሉ ትእዛዙን ለማስቆም ባቀረበው መከራከሪያ ላይ ፣ የትራምፕን ስም ከህንፃው ላይ ማንሳት ቀደም ሲል ይፋ ባልተደረገ የማዕከሉ የመተዳደሪያ ደንብ ለውጥ ምክንያት ለዕድሳት የተሰበሰበ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እንዲመለስ ሊያስገድድ ይችላል ብሏል።

ለፍርድ ቤት የቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው ይህ አንቀጽ የተቀመጠበት ምክንያት "ለማዕከሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የለገሱ ወይም ለመለገስ ያሰቡ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑት 'ትራምፕ' የሚለው ስም በህንፃው ላይ መኖሩን ተከትሎ ነው" በሚል ነው።

​ይሁን እንጂ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ይህ ለውጥ መቼ፣ እንዴት እና የት እንደተደረገ በሰነዱ ላይ የተገለጸ ነገር የለም። የኬኔዲ ማዕከል ደንቡ መቼ እንደተቀየረ እና በትክክል ምን ያህል ገንዘብ አደጋ ላይ እንደወደቀ ለኤን ቢ ሲ ኒውስ ለቀረበለት ጥያቄ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

10 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.