በዓለም ዋንጫ የአፍሪካ አህጉር ተወካዮች የሆኑት ኮትዲቯር እና ቱኒዚያ ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባሉ
#ethiopia | በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉት ኮትዲቯር እና ቱኒዚያ ዛሬ ምሽት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
በዚህም መሠረት የዝሆኖቹ ሀገር ኮትዲቯር ከደቡብ አሜሪካዋ ጠንካራ ተጋጣሚ ኢኳዶር ጋር ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ትገናኛለች።
በአውሮፓ ታዋቂ ሊጎች ውስጥ የሚጫወቱ በርካታ ባለክህሎት ተጫዋቾችን የያዘችው ኮትዲቯር ለኢኳዶር ከባድ ፈተና እንደምትሆን በስፋት ተገምቷል።
ሌላኛዋ የአፍሪካ ተወካይ ሰሜን አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ በበኩሏ ከጠንካራዋ የአውሮፓ ሀገር ስዊድን ጋር ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ፍልሚያዋን ታደርጋለች።
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በዓለም እግር ኳስ ግዙፍ ስም ያላት ጀርመን ከካራካኦ ጋር የምታደርገው ጨዋታ በብዙዎች ዘንድ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ኔዘርላንድ ከእስያዋ ተስፈኛ ሀገር ጃፓን ጋር የምታደርገው ጨዋታ የዛሬው ምሽት ሌላኛው አጓጊ መርሃ ግብር ነው።
ትናንት ምሽት በተከናወኑ ጨዋታዎች አውስትራሊያ ቱርኪዬን ሁለት ለባዶ ያሸነፈች ሲሆን ስኮትላንድ በበኩሏ ሃይቲን አንድ ለባዶ በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ኩራት የሆነችው ሞሮኮ ከዓለም እግር ኳስ ኃያሏ ብራዚል ጋር እንዲሁም ኳታር ከስዊዘርላንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በተመሳሳይ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
#worldcup2026 #africanfootball #cotedivoire #tunisia #fifaworldcup #footballnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 hours ago