ኪራይ ዝም ብሎ አይጨመርም‼️
አከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ብቻ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይችሉም - ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ‼️
የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና በዘርፉ የሚታዩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለመፍታት በተጀመረው የዲጂታል ምዝገባ ሂደት እስካሁን ወደ አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ቤቶች ወደ ሲስተሙ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ይህ አዲስ አሰራር በቤት ኪራይ ዋጋ ላይ ያለ አግባብና ያለ ምንም ምክንያታዊ መነሻ ይደረግ የነበረውን ያልተገባ ጭማሪ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
ወደ ዲጂታል ቋቱ የገቡት እነዚህ የኪራይ ቤቶች በየትኛው ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ፣ አልፎ ተርፎም በየትኛው ብሎክ ላይ እንደሚገኙ ሙሉ መረጃቸው በግልጽ የሚታወቅበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ይህም አከራዮች ቤታቸውን ስለማከራየታቸው መረጃ የመደበቅ ዕድል እንዳይኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን ኃላፊዋ አብራርተዋል።
በአዲሱ አሰራር መሠረት አከራዮች በራሳቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት ብቻ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይችሉም።
መንግሥት በየዓመቱ አንድ ጊዜ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የገበያ ጥናት ካካሄደ በኋላ፣ የገበያ ዕድገት መኖሩ ሲረጋገጥ በየዓመቱ ሰኔ 30 ላይ በሚያወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት የዋጋ ጭማሪውን በፐርሰንት (በመቶኛ) ይወስናል።
ኃላፊዋ ለአብነት ሲያስረዱም፤ የአንድ ቤት ኪራይ 1 ሺህ ብር ቢሆን፣ አከራዩ በራሱ ፈቃድ ዋጋውን ማሳደግ አይችልም።
በመንግሥት ውሳኔ መሠረት የሚፈቀደው ጭማሪ 10 በመቶ ወይም 100 ብር ብቻ ከሆነ፣ ዋጋውን ወደ 1 ሺህ ብር ማሳደግ የሚቻለው በዚያው ሕጋዊ አሰራር መሠረት ብቻ ነው።
ከዚህ ውጭ የተጋነነ ዋጋ የሚጨመርበት ምንም ዓይነት አሰራር እንደማይኖር አስገንዝበዋል።
የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ ከተጀመረ በአሁኑ ወቅት የሁለት ዓመት ገደማ መሙላቱን የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ ቀደም ሲል ምዝገባው የሚከናወነው ሁለቱም ወገኖች በአካል በመቅረብ እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ላይ ግን ቤቶቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ቋት የገቡ በመሆናቸው፣ እንግልትን ለማስቀረት የውል ማደስ ሥራውን በኢንተርኔት (ኦንላይን) ለማከናወን የሚያስችል ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
በዚህም መሠረት አከራይና ተከራይ ዋጋ ሳይጨመርበት ባለው የውል ስምምነት መቀጠል ከፈለጉ፣ ውላቸውን በኦንላይን በቀላሉ ማደስ ይችላሉ።
የውል ጊዜው በማብቃቱ ምክንያት ብቻ አከራዮች ተከራዩን አስወጥተው ሌላ ሰው ለማስገባት ቢሞክሩ እንኳ፣ ዋጋ ጨምረው ማከራየት የማይችሉ በመሆኑ ተከራዮች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ይደረግብኛል በሚል ስጋት ሊገቡ እንደማይገባ ኃላፊዋ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የገበያ ጥናት ሥራው በንቃት እየተከናወነ እንደሚገኝና የመጨረሻው ውጤት እንደደረሰም ይፋዊ መመሪያዎች በተከታታይ ተግባራዊ መደረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ተከራዮች መብታቸውን በደንብ ሊያውቁና ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ያሳሰቡት መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ፤ አከራዮች ዋጋ ጨምሩ ስላሏቸው ብቻ ያለምንም ሕጋዊ መነሻ ክፍያ መጨመር እንደሌለባቸው አሳስበዋል።
አብዛኞቹ ውሎች ጊዜያቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ በመሆኑ፣ በውል ስምምነት ውስጥ እያሉ ዋጋ መጨመር ፈጽሞ እንደማይፈቀድም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ በየሁለት ዓመቱ የኪራይ ውልን በተገቢው መንገድ ማደስ ግዴታ ሲሆን፣ አከራዮችም መብትና ግዴታቸውን ለይተው በማወቅ ሕጋዊ አሰራሩን እንዲያከብሩ ጥሪ ቀርቧል።
መንግሥት በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን ዘላቂ ችግር ለመቅረፍ የጀመረውን የአሰራርና የቴክኖሎጂ ማሻሻያ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትም ተገልጿል።#amn
Seledadotio

18 hours ago