Logo
FastMereja
አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ በዶፒንግ ምርመራ የአራት ወር እገዳ ተጣለባት

​#fastmereja | የዓለም 5,000 እና 10,000 ሜትር የቀድሞ ሻምፒዮን አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣ በዶፒንግ ምርመራ ወቅት በሰውነቷ ውስጥ "ሌትሮዞል" የተባለ ንጥረ ነገር በመገኘቱ የአራት ወር እገዳ ተላልፎባታል።

እንደ አትሌቲክስ ዊክሊ ዘገባ በ​አትሌቷ የተገኘው ንጥረ ነገር የታዘዘላትን የህክምና ችግር ለመቆጣጠር ትጠቀምበት የነበረ መሆኑን በማስረጃ ማቅረቧን ተከትሎ፣ የዓለም አትሌቲክስ ጥብቅና ክፍል (AIU) ከረዥም ጊዜ ቅጣት ይልቅ የአራት ወር እገዳን እንዲወስን ስምምነት ላይ ተደርሷል።

​የ29 ዓመቷ አትሌት ጉዳፍ፣ ይህን ተከትሎ የ2026 የውድድር ዓመትን የትራክ ውድድሮች በሙሉ እንደማትሳተፍ ተገልጿል።

​የአትሌቲክስ ጥብቅና ክፍሉ ባወጣው መግለጫ፣ ጉዳፍ ምርመራው መገኘቱን አምና Case Resolution Agreement እንደፈረመች አስታውቋል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.