Logo
SeledaPost
በፌስቡክ እና በሌሎች የሜታ (Meta) አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል አጋጠመ!

ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፌስቡክ፣ የኢንስታግራም እና የሜሴንጀር ተጠቃሚዎች ከፍተኛ የአገልግሎት መቋረጥ እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት እያደረጉ ይገኛሉ።

ምን ተከሰተ?

ብዙሃኑ ተጠቃሚዎች ከበይነ-መረብ አካውንቶቻቸው በራሱ ጊዜ Log out እየሆኑባቸው ሲሆን፥ ተመልሰው ለመግባት በሚሞክሩበት ወቅትም የሚከተሉትን የስህተት መልዕክቶች እያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፦

- Something went wrong” የሆነ የተሳሳተ ነገር ተከስቷል) *Query error” (የጥያቄ ስህተት) ከተለመደው የፌስቡክ መተግበሪያ በተጨማሪ የ Messenger እና የInstagram አገልግሎቶችም ተመሳሳይ እክል እንደገጠማቸው ታውቋል።

ምን ማድረግ ይኖርብዎታል? ችግሩ ከእርስዎ ስልክ ወይም የኢንተርኔት ግንኙነት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከራሱ ከሜታ (Meta) ሰርቨር የመነጨ በመሆኑ፦

1. አይደናገጡ፦አካውንቴ ተጠለፈ (Hack ተደረገ) ብለው እንዳይሰጉ።

2. ይጠብቁ፦የሜታ የቴክኒክ ባለሙያዎች ችግሩን ቀርፈው አገልግሎቱን ወደ ነበረበት እስኪመልሱ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ ብልህነት ነው።

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.