Logo
Getu Temesgen
አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ አበባ ከተማ መሰጠት ተጀመረ
#ethiopia | ETH የሚል ዓለም አቀፋዊ ኮድ የያዘዉ አዲሱ ሰሌዳ በአዲስ አበባ ሰሌዳ ለመዉሰድ ተመዝግበው እየተጠባበቁ ባሉ አዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ ከሰኔ 4 ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ በላይነህ አዲሱ ሰሌዳ ሀገራዊ ይዘት ያለዉ ፣ ፎርጂድ የማይሰራ ፣የሀብት ብክነትን የሚቀነስ ፣ለህግ ማስከበር የሚመች ፣ስርቆትንና ህገወጥ ዝዉዉርን ለመከላከል የሚረዳ መሆኑን መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል።

የመጀመሪያዉ ሰሌዳ ባለስልጣኑ ካሉት 11 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች አንዱ በሆነዉ የየካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መሰጠቱ ተገልጿል ።

በብዙሃን ትራንስፓርት እና የግል ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ዋጋዉ ላይ ልዩነት እንደሚኖረዉ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ቁጥጥር አማካሪ አቶ አሰፋ ሀዲስ ተናግረዋል ።

አዲሱ ሰሌዳ ተሽከርካሪዉ እስኪወገድ ድረስ የሚያገለግል መሆኑን የገለፀዉ ባለስልጣኑ ከ800 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች መኖራቸዉንና ሰሌዳዉ ተወስዶ መቼ ይጠናቀቃል የሚለዉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚወሰን መሆኑን ገልጿል ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተወሰነ ከተሄደበት በኃላ በክልሎችም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በሚያስቀምጣቸው የጊዜ እቅድ ሰሌዳዉን የመቀየር ሂደቱ እንደሚተገበር ተገልጿል ያለው ብስራት ኤፍ ኤም ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.